1
መጽሐፈ መክብብ 8:15
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ስለዚህ ሰው በዚህ ዓለም ሲኖር የተሰጠው ዕድል ፈንታ መብላት፥ መጠጣትና ራሱን ማስደሰት መሆኑን አረጋገጥኩ፤ እግዚአብሔር በዚህ ዓለም በሰጠው ዘመን፥ ሰው ሁሉ ሠርቶ ያገኘውን ሀብት በዚህ ዐይነት ይደሰትበታል።
Compare
Explore መጽሐፈ መክብብ 8:15
2
መጽሐፈ መክብብ 8:12
ይኸውም ኃጢአተኞች መቶ ጊዜ ወንጀል ቢሠሩም ለረጅም ዘመን ይኖራሉ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔርን ለሚፈሩና ለሚያከብሩ ሁሉ ነገር እንደሚሰምርላቸው ዐውቃለሁ።
Explore መጽሐፈ መክብብ 8:12
3
መጽሐፈ መክብብ 8:6
ሕይወት አስቸጋሪ ቢሆንም ለሁሉም ነገር ጊዜና ቦታ አለው።
Explore መጽሐፈ መክብብ 8:6
4
መጽሐፈ መክብብ 8:8
የሕይወትን እስትንፋስ ለማስቀረትና የሞትን ቀን ለመለወጥ የሚችል ማንም የለም፤ ማንም ሰው ከጦር ሜዳ መሰናበት እንደማይችል ክፋትም ክፉ ሠሪዎችን አይለቃቸውም።
Explore መጽሐፈ መክብብ 8:8
5
መጽሐፈ መክብብ 8:11
ሰዎች ሆን ብለው ወንጀል የሚሠሩት ለምንድን ነው? የዚህ ምክንያት ሌላ ሳይሆን ወንጀል በሚሠሩ ሰዎች ላይ ፈጣን የቅጣት ፍርድ ባለመሰጠቱ ነው።
Explore መጽሐፈ መክብብ 8:11
6
መጽሐፈ መክብብ 8:14
በምድር ላይ የሚደረግ ከንቱ ነገር አለ፤ አንዳንድ ጊዜ ደጋግ ሰዎች ለክፉ ሰዎች የሚገባውን ቅጣት ይቀበላሉ፤ ክፉ ሰዎች ደግሞ ለደጋግ ሰዎች የሚገባውን ዋጋ ያገኛሉ፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ነው አልኩ።
Explore መጽሐፈ መክብብ 8:14
7
መጽሐፈ መክብብ 8:7
ወደፊት የሚሆነውን ነገር ለይቶ የሚያውቅ ሰው የለም፤ “ይህ ይሆናል” ብሎ የሚነግረውስ ማነው?
Explore መጽሐፈ መክብብ 8:7
Home
Bible
Plans
Videos