መከራንና ሥቃይን መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?ናሙና

መከራንና ሥቃይን መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?

ቀን {{ቀን}} ከ18

ልዩ ልዩ መከራና የሥቃይ ዓይነቶች

“ወደ መቄዶንያ በመጣን ጊዜ፣ ከየአቅጣጫው መከራ ደረሰብን እንጂ ሰውነታችን ዕረፍት አላገኘም፤ ከውጭ ጠብ፣ ከውስጥ ደግሞ ፍርሀት ነበረብን” ( 2 ቆሮንቶስ 7:5 )።

ጳውሎስ ወንጌልን ሲሰብክ ብዙ ችግር ገጥሞታል። ከችግሮቹ መካከል አንዳንዶቹ ከጉዞው ጋር የተያያዙ ነበሩ፥ ሦስት ጊዜ መርከብ መሰበር፣ በባሕር ላይ አደጋ፣ በወንዞች ሙላት አደጋ እና በዘራፊዎች አደጋ ውስጥ መሆን.... እንዲሁም፤ ሥራውን የሚቃወሙ ሰዎች የበለጠ ሥቃይ አስከትለውበታል፤ በድንጋይ ተወግሮ፣ በበትር ተደብድቦ፣ ብዙ ጊዜ ተገርፎ፣ ታስሮ.... ይህ አስገራሚ የመከራ ዝርዝር ከ2ኛ ቆሮንቶስ 11፡23-27 የምንመለከተው ስለ “ውጫዊ” መከራዎች ነው። እነዚህ ነገሮች የተፈጠሩት በጳውሎስ ጠላቶች ወይም በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ነው።

ነገር ግን በቁጥር 28 ላይ አንድ ተጨማሪ ነገር ጨምሯል፡- “ሌላውን ነገር ሳልቈጥር፣ ዕለት ዕለት የሚያስጨንቀኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሐሳብ ነው።” ይህ "ውስጣዊ ትግል" ነው።

በ2ኛ ቆሮንቶስ 7፡5 ደግሞ ስለ "በውጭ ስላሉ ግጭቶች፣ በውስጥ ፍርሃት" ይናገራል። አንዳንድ አማኞች በእምነታቸው ምክንያት በጭራሽ አይሰደዱም። ነገር ግን "በውስጣቸው ፍርሐቶች" ሊገጥሟቸው ይችላሉ። ሰይጣን ደስታቸውን እና በጌታ ላይ ያላቸውን እምነት ሊነጥቃቸው ይፈልጋል። ስለ ወረርሽኝ፣ በህብረተሰቡ ውስጥ በእግዚአብሔር ላይ ስለሚነሣው ተቃውሞ፣ ስለሚወዷቸው ሰዎች ወይም ስለ ክርስቲያን ወንድሞቻቸው አስቸጋሪ ጊዜያት እያለፉ ስለመሆናቸው እንዲጨነቁ ለማድረግ ይሞክራል።.

በውጫዊ ወይም በውስጣዊ ጥቃቶች ተጎድተዋል?

ስለዚህ እቅድ

መከራንና ሥቃይን መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?

ሐዋርያው ​​ጳውሎስ ለአንባቢዎቹ “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” (የሐዋርያት ሥራ 14:22) ይላል። የሐዋርያት ሥራን ማንበብ ወይም በዓለም ዙሪያ ካሉ ክርስቲያኖችን ምስክርነት መስማት፣ የዚህን ቃል እውነት አረጋግጠዋል። አማኞች ተቃውሞ እና ስደት ይደርስባቸዋል። ምናልባት እርሶም መከራ አጋጥሞት ይሆናል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ፣ ልናበረታታዎት እና በመከራን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ማስተማር እንፈልጋለን።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org