መከራንና ሥቃይን መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?ናሙና

ሌሎች ለሥቃይ ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች
‘’ስለ እግዚአብሔር ሲል የግፍ መከራን የሚቀበል ሰው ምስጋናን ያገኛል። ክፉ ሥራ ሠርታችሁ ብትቀጡና ብትታገሡ ምን ምስጋና ይኖራችኋል? (1 ጴጥሮስ 2:19-20)።
በምንሰቃይበት ጊዜ እነዚህን ሀዘኖች የምንጸናበትን ምክንያት በጥንቃቄ መመርመር አለብን። ትናንት እንደምናነበው፣ ክርስቲያኖች ብዙውን ጊዜ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሲኖሩ ይጠቃሉ፣ ምክንያቱም ሰይጣን ይህን ይጠላል። ይህ ስለ ኢየሱስ የምንቀበለው መከራ ስለሆነ ነው፤ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋን እንቀበላለን። ‘’መልካም ሥራ ሠርታችሁ መከራ ብትቀበሉና ብትታገሡ ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋና ያስገኝላችኋል’’ (1 ጴጥሮስ 2: 20) ይናገራል። በጸጋ ካልሆነ በፍፁም ደስ የሚል አይደለም፣ ነገር ግን አናፍርበትም። ጴጥሮስም በመልእክቱ ለዚህ እንደተጠራን ገልጾልናል።
ይሁን እንጂ ለችግሮቻችን ሌሎች ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ! ሐዋርያው ጴጥሮስ እንዳመለከተው፣ የራሳችንን ግትርነት፣ ስንፍና ወይም ኃጢአት የሚያስከትለውን መዘዝ ልንጋፈጥ እንችላለን። ጉዳዩ ይህ ከሆነ እንደቃሉ ራሳችንን መለወጥ አለብን! በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ "ስለእምነታችን በግፍ እየተሠቃየን" አይደለንም። ይህ እኛ የኢየሱስ ተከታይ ከመሆናችን ጋር ምንም ግንኙነት የለውም።
ልንመረምረው የሚገባን ሌላው አማራጭ አምላክ ሊያርመን ሊገስጸን ይፈልግ እንደሆነ ነው። በኃጢአት የምንኖር ከሆነ ዕብራውያን 12፡10 እንደሚለው “ለጥቅማችን ሊገሥጸን” ይችላል። ይህ ያማል፣ ግን አስፈላጊ ነው፣ የበለጠ ቅዱሳን ለመሆን ከዚህ ትምህርት መማር አለብን። ልባችንን ወደ እርሱ እየሳበ መሆኑ ማመላከቻ ነው።
እየተሰቃዩ ከሆነ፣ ስቃይዎ ከየት እንደመጣ ለማሰብ ትንሽ ጊዜ ይውሰዱ!"
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ

ሐዋርያው ጳውሎስ ለአንባቢዎቹ “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” (የሐዋርያት ሥራ 14:22) ይላል። የሐዋርያት ሥራን ማንበብ ወይም በዓለም ዙሪያ ካሉ ክርስቲያኖችን ምስክርነት መስማት፣ የዚህን ቃል እውነት አረጋግጠዋል። አማኞች ተቃውሞ እና ስደት ይደርስባቸዋል። ምናልባት እርሶም መከራ አጋጥሞት ይሆናል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ፣ ልናበረታታዎት እና በመከራን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ማስተማር እንፈልጋለን።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org