1
ወደ ሮም ሰዎች 3:23-24
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።
Vergelyk
Verken ወደ ሮም ሰዎች 3:23-24
2
ወደ ሮም ሰዎች 3:22
እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤
Verken ወደ ሮም ሰዎች 3:22
3
ወደ ሮም ሰዎች 3:25-26
እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፥ ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በኢየሱስም የሚያምነውን እንዲያጸድቅ አሁን በዚህ ዘመን ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው።
Verken ወደ ሮም ሰዎች 3:25-26
4
ወደ ሮም ሰዎች 3:20
ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና።
Verken ወደ ሮም ሰዎች 3:20
5
ወደ ሮም ሰዎች 3:10-12
እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ፤ አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፤ ሁሉ ተሳስተዋል፥ በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል፤ ቸርነት የሚያደርግ የለም፥ አንድ ስንኳ የለም።
Verken ወደ ሮም ሰዎች 3:10-12
6
ወደ ሮም ሰዎች 3:28
ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና።
Verken ወደ ሮም ሰዎች 3:28
7
ወደ ሮም ሰዎች 3:4
እንዲህ አይሁን፤ በቃልህ ትጸድቅ ዘንድ ወደ ፍርድ በገባህም ጊዜ ትረታ ዘንድ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ሰው ሁሉ ውሸተኛ ከሆነ እግዚአብሔር እውነተኛ ይሁን።
Verken ወደ ሮም ሰዎች 3:4
Tuisblad
Bybel
Leesplanne
Video's