1
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ ዓላማውም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
Thelekisa
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:38-39
ይህንን ተረድቼአለሁ፤ ሞትም ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ገዢዎችም ቢሆኑ፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ጥልቀትም ቢሆን፥ ሌላ ፍጥረትም ቢሆን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም።
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 8:38-39
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:26
እንዲሁም ደግሞ መንፈስ በድካማችን ይረዳናል፤ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በቃላት ሊገለጥ በማይችል መቃተት ለእኛ ያማልድልናል፤
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 8:26
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:31
እንግዲህ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 8:31
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:1
ስለዚህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም።
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 8:1
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:6
ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 8:6
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:37
በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 8:37
8
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:18
የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ወደ ፊት ለእኛ ከሚገለጥልን ክብር ጋር ሲነጻጸር ምንም ዋጋ እንደሌለው እቆጥረዋለሁ።
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 8:18
9
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:35
ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማን ነው? መከራ ወይስ ሥቃይ፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ረሃብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ አደጋ፥ ወይስ ሰይፍ?
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 8:35
10
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:27
ልቦችንም የሚመረምረው እርሱ የመንፈስ ሐሳብ ምን እንደሆነ ያውቃል፥ ምክንያቱም መንፈስ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ያማልዳልና።
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 8:27
11
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:14
በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ፥ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 8:14
12
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:5
እንደ ሥጋ የሚኖሩ አእምሮአቸው የሥጋን ነገር እንዲያስብ ያደርጋሉና፥ እንደ መንፈስ የሚኖሩ ግን አእምሮአቸው የመንፈስን ነገር እንዲያስብ ያደርጋሉ።
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 8:5
13
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:32
ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው እርሱ፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 8:32
14
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:16-17
የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን መንፈሱ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክርልናል። ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ከእርሱ ጋር የክብሩ ተካፋዮች እንድንሆን ከእርሱ ጋር መከራ ብንቀበል የእግዚአብሔር ወራሾችና ከክርስቶስም ጋር አብረን ወራሾች ነን።
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 8:16-17
15
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:7
ስለ ሥጋ ማሰብ የእግዚአብሔር ጠላት መሆን ነው፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም አይችልም፥
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 8:7
16
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:19
ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ በታላቅ ናፍቆት ይጠባበቃልና።
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 8:19
17
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:22
እስከ አሁን ድረስ ፍጥረት ሁሉ አብሮ በመቃተትና በምጥ ሥቃይ እንደሚኖር እናውቃለንና።
Phonononga ወደ ሮሜ ሰዎች 8:22
Ekuqaleni
IBhayibhile
Izicwangciso
Iividiyo