ክርስቶስ የእኛ አሸናፊSample

ክርስቶስ የእኛ አሸናፊ
ከመዝሙረ ዳዊት 68:7–18 አሸናፊ በሆነልን በክርስቶስ በኩል ከሀጢአትና ከሞት ነፃ በማውጣት ህዝቡን የሚታደገውን፤ በዓለም፣ በስጋና በሰይጣን መልክ ከሚገለጡት ጠላቶቻችን የሚጠብቀንን እና አንድ ቀን ወደ ዘላለማዊ ቤት ወደ እርሱ በደህና የሚያደርሰንን የእግዚአብሔርን ኃይል እናያለን፡፡
በጣም በሚያስፈራ ገደላማ ተራራ ላይ የሚወጡ ሰዎች ራሳቸውን በገመድ በአንድነት ያስሩታል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከመካከላቸው አንዱ በድንገት ቢንሸራተት ያልተንሸራተተው ሾልኮ የወጣውን ገደል ላይ እንዳይወድቅ ስለሚያደርገው ነው። በማንኛውም ተራራ ወጪ ቡድን ውስጥ ሁልጊዜ በጥንካሬው፣ በዕውቀቱና በልምዱ ለቡድኑ የመረጋጋትና የደህንነት ስሜት እንዲሰማቸው የሚያደርግ ጀግና መሪ አለ፡፡
ዛሬ ላይ እንዳለ ክርስቲያን ለአንተና ለእኔ በዚህች በወደቀችና አደገኛ በሆነች ዓለም በምንወጣው ገደላማና አቀበት የበዛበት ህይወት በዕብራውያን 12:2 ላይ የተገለፀው የእኛ ጀግና ተራራ ወጪ የእምነታችን ራስና ፍፁም አድራጊ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡ እርሱ በየዕለቱ ባለን የዘላለም ጉዞ በፍቅሩ እና በመለኮታዊ ብርታትና ጥበብ የሚመራን አሸናፊው ተራራ ወጪ ነው፡፡ ብንንሸራተት እንኳን የፍቅሩ ገመድ በቦታችን አፅንቶ በደህና ወደ ቤቱ ያደርሰናል፡፡
ምናልባት በዚህ ዕቅድ ውስጥ ስታልፍ ራስህን በዓለማችን ሁኔታ እጅግ እየተጨነቅክና እየተሸበርክ ልታገኘው እና በህይወትህ ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ ልትገኝ ትችል ይሆናል፡፡ በየዕለቱ በሚዲያ ዘገባዎች በዓለም ላይ ስላሉ ጦርነቶች፣ አስጨናቂ ስለሆኑ የአየር ለውጥና የተፈጥሮ አደጋዎች፣ ስለሚያስጨንቀው የግሽበት ሁኔታ እና እኚህ ሁሉ ከአንተ አቅም በላይ ስላሉ ተግዳሮቶችን በብዙ ስጋት ሆነህ ትሰማለህ፡፡
የዓለማችን ሁኔታ ምንም ይሁን ምንም ዓይነት ተግዳሮቶችም በህይወትህ ይግጠሙህ ግን የዚህ መልዕክት የወንጌል እውነት እንዲያበረታህ ፍቀድ ይኸውም በአሸናፊው በክርስቶስ ኢየሱስ ስራ ምክንያት እግዚአብሔር ለዘላለም ከሀጢአትና ከሞት እስራት ነፃ በማውጣት ታድጎሃል፤ አንተ በየቀኑ በፍቅሩና በአስደናቂው ፀጋ እየተጠበቅህ ነው፤ እግዚአብሔርም አንድ ቀን ወደ ዘላለማዊ ቤት ወደ እርሱ በደህና ያደርስሃል፡፡
Scripture
About this Plan

በአሸናፊው በክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር ለዘለዓለም ከሀጢአትና ከሞት ነፃ አውጥቶ ጠብቆናል፤ አሁንም በዚህ በወደቀ ዓለም ይጠብቀናል፤ አንድ ቀንም ወደ ራሱ በደህና ያደርሰናል፡፡
More
Related Plans

Prayer Altars: Embracing the Priestly Call to Prayer

Journey With Jesus: 3 Days of Spiritual Travel

Sickness Can Draw You and Others Closer to God, if You Let It – Here’s How

Here Am I: Send Me!

Journey Through Proverbs, Ecclesiastes & Job

Journey Through Jeremiah & Lamentations

Live Like Devotional Series for Young People: Daniel

How Stuff Works: Prayer

The Making of a Biblical Leader: 10 Principles for Leading Others Well
