1
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:3-4
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
አንተም እንደዚህ በሚያደርጉ ላይ የምትፈርድ ያንንም የምታደርግ ሰው ሆይ! ከእግዚአብሔር ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃልን? ወይስ የቸርነቱን፥ የቻይነቱን፥ የታጋሽነቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን? የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሓ ሊመራህ እንደሆነ አታውቅምን?
مقایسه
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:3-4 را جستجو کنید
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:1
ስለዚህ አንተ የምትፈርድ ሰው ሆይ! የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው ላይ በምትፈርድበት ነገር በራስህ ላይ ትፈርዳለህ፤ ፈራጅ የሆንከው አንተ ያንኑ ታደርጋለህና።
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:1 را جستجو کنید
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:11
በእግዚአብሔር ዘንድ ማዳላት የለምና።
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:11 را جستجو کنید
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:13
በእግዚአብሔር ፊት ሕግን የሚፈፅሙት ይጸድቃሉ እንጂ ሕግን የሚሰሙት አይጸድቁምና።
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:13 را جستجو کنید
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:6
እርሱ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይሰጠዋል፤
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:6 را جستجو کنید
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:8
በራስ ወዳዶች፥ ለእውነት በማይታዘዙት ነገር ግን ለዐመፃ በሚታዘዙት ላይ ቁጣና መቅሠፍት ይመጣባቸዋል።
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:8 را جستجو کنید
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:5
ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሓ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቁጣ ቀን በራስህ ላይ ቁጣን ታከማቻለህ።
ወደ ሮሜ ሰዎች 2:5 را جستجو کنید
خانه
كتاب مقدس
برنامههای مطالعه
ویدیوها