1
የሉቃስ ወንጌል 3:21-22
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ሕዝቡም ሁሉ በተጠመቁ ጊዜ ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ፤ ሲጸልይም ሳለ ሰማይ ተከፈተ፤ መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ፤ “የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል፤” የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ።
مقایسه
የሉቃስ ወንጌል 3:21-22 را جستجو کنید
2
የሉቃስ ወንጌል 3:16
ዮሐንስ ለሁሉም እንዲህ ብሎ መለሰ፦ “እኔስ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ነገር ግን ከእኔ የሚበረታ ይመጣል፤ የጫማውን ጠፍር መፍታት እንኳ አይገባኝም፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፤
የሉቃስ ወንጌል 3:16 را جستجو کنید
3
የሉቃስ ወንጌል 3:8
እንግዲህ ለንስሓ የሚገቡ ፍሬዎች አፍሩ፤ በልባችሁም ‘አብርሃም አባት አለን፤’ አትበሉ፤ ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር እንደሚችል እነግራችኋለሁና።
የሉቃስ ወንጌል 3:8 را جستجو کنید
4
የሉቃስ ወንጌል 3:9
ቀድሞውንም እንኳ ምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።”
የሉቃስ ወንጌል 3:9 را جستجو کنید
5
የሉቃስ ወንጌል 3:4-6
የነቢዩ ኢሳይያስ ቃላት በሚገኘበት መጽሐፍ እንደተጻፈው፦ “በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፤ የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጥርጊያውንም አቅኑ፤ ጐድጓዳው ሁሉ ይሙላ፤ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፤ ጠማማውም መንገድ ቀና ይሁን፤ ሸካራውም መንገድ የተስተካከለ ይሁን፤ ሥጋም የለበሰ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ፤”
የሉቃስ ወንጌል 3:4-6 را جستجو کنید
خانه
كتاب مقدس
برنامههای مطالعه
ویدیوها