1
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:17
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል!
مقایسه
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:17 را جستجو کنید
2
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:21
እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን ስለ እኛ ኃጢአት የሌለበትን እርሱን ኃጢአት አደረገው።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:21 را جستجو کنید
3
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:7
የምንኖረው በእምነት እንጂ በማየት አይደለም።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:7 را جستجو کنید
4
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:18-19
ይህ ሁሉ የሆነው፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን፥ የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህ እግዚአብሔር የሰዎችን በደል ሳይቆጥርባቸው በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋር አስታርቋል፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኑሯል።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:18-19 را جستجو کنید
5
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:20
ስለዚህ እግዚአብሔር ጥሪውን የሚያቀርበው በእኛ በኩል በመሆኑ፥ እኛ ለክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ስለ ክርስቶስ ሆነን “ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ” ብለን እንለምናለን።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:20 را جستجو کنید
6
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:15-16
በሕይወትም ያሉት፥ ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ፥ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ እርሱ ስለ ሁሉ ሞተ። ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሰብአዊ አመለካከት እንደምናየው አድርገን አንመለክትም፤ ክርስቶስንም በዚህ መልክ ተመልክተነው የነበርን ብንሆን እንኳን፥ ከእንግዲህ ወዲህ ግን በዚህ መልክ አይደለም የምናውቀው።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:15-16 را جستجو کنید
7
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:14
አንዱ ስለ ሁሉ እንደ ሞተ እርግጠኞች በመሆናችን፥ የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል፤ ይህ በመሆኑም ሁሉ ሞተዋል።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:14 را جستجو کنید
خانه
كتاب مقدس
برنامههای مطالعه
ویدیوها