መዝሙረ ዳዊት 42:1-3
መዝሙረ ዳዊት 42:1-3 አማ2000
አቤቱ፥ ፍረድልኝ፥ ከጽድቅ ከወጡ ሕዝብም በቀሌን ተበቀል። ከዐመፀኛና ከሸንጋይ ሰው አድነኝ። አንተ አምላኬ፥ ኀይሌም ነህና፥ ለምን ትተወኛለህ? ጠላቶቼ ቢያስጨንቁኝ ለምን አዝኜ እመለሳለሁ? ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክ፤ እነርሱም ይምሩኝ፥ አቤቱ ወደ መቅደስህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ።






