YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 1

1
የፍ​ጥ​ረት ታሪክ
1በመ​ጀ​መ​ሪያ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ፈጠረ። 2ምድር ግን ባዶ ነበ​ረች፤ አት​ታ​ይ​ምም#“አት​ታ​ይም” በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ነበር፤ የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ችም አል​ነ​በ​ረ​ችም፤ ጨለ​ማም በው​ኃው ላይ ነበረ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በው​ኃው ላይ ይሰ​ፍፍ ነበር። 3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ብር​ሃን ይሁን” አለ፤ ብር​ሃ​ንም ሆነ።
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብር​ሃኑ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በብ​ር​ሃ​ኑና በጨ​ለ​ማው መካ​ከል ለየ። 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብር​ሃ​ኑን “ቀን፥” ጨለ​ማ​ው​ንም “ሌሊት” ብሎ ጠራው። ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ አን​ደኛ ቀንም ሆነ። 6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በው​ኃው መካ​ከል ጠፈር ይሁን፤ በው​ኃና በውኃ መካ​ከ​ልም ይለይ” አለ፤ እን​ዲ​ሁም ሆነ።
7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጠፈ​ርን አደ​ረገ፤ ከጠ​ፈር በላ​ይና ከጠ​ፈር በታች ያሉ​ት​ንም ውኆች ለየ። 8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያን ጠፈር “ሰማይ” ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ ሁለ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።
9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሰ​ማይ በታች ያለው ውኃ በአ​ንድ ስፍራ ይሰ​ብ​ሰብ፥ የብ​ሱም ይገ​ለጥ አለ፤ እን​ዲ​ሁም ሆነ። ከሰ​ማይ በታች ያለው ውኃም በመ​ጠ​ራ​ቀ​ሚ​ያው ተሰ​በ​ሰበ፤ የብ​ሱም ተገ​ለጠ። 10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የብ​ሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፤ የውኃ መጠ​ራ​ቀ​ሚ​ያ​ው​ንም “ባሕር” ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። 11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም “ምድር በየ​ዘሩ፥#“በየ​ዘሩ” በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በየ​ወ​ገ​ኑና በየ​መ​ልኩ ዘር የሚ​ሰጥ ቡቃ​ያን፥ በም​ድ​ርም ላይ በየ​ወ​ገኑ ዘሩ በው​ስጡ የሚ​ገ​ኘ​ው​ንና ፍሬ የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን ዛፍ ታብ​ቅል” አለ፤ እን​ዲ​ሁም ሆነ። 12ምድ​ርም በየ​ዘሩ፥#“በየ​ዘሩ” በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በየ​ወ​ገ​ኑና በየ​መ​ልኩ የሚ​ዘራ ቡቃ​ያን፥ በም​ድር ላይ በየ​ወ​ገኑ ዘሩ በው​ስጡ የሚ​ገ​ኘ​ው​ንና ፍሬ የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን ዛፍ አበ​ቀ​ለች። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። 13ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ። ሦስ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።
14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “በም​ድር ላይ ያበሩ ዘንድ፥ በቀ​ንና በሌ​ሊ​ትም ይለዩ ዘንድ ብር​ሃ​ናት በሰ​ማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለም​ል​ክ​ቶች፥ ለዘ​መ​ናት፥ ለዕ​ለ​ታት፥ ለዓ​መ​ታ​ትም ይሁኑ። 15በም​ድር ላይ ያበሩ ዘንድ፥ በሰ​ማይ ጠፈር ለማ​ብ​ራት ይሁኑ፤” እን​ዲ​ሁም ሆነ። 16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሁለት ታላ​ላቅ ብር​ሃ​ና​ትን አደ​ረገ፤ ትልቁ ብር​ሃን ቀንን እን​ዲ​መ​ግብ፥ ትንሹ ብር​ሃ​ንም ከከ​ዋ​ክ​ብት ጋር ሌሊ​ትን እን​ዲ​መ​ግብ አደ​ረገ። 17እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰ​ማይ ጠፈር አኖ​ራ​ቸው፤ 18መዓ​ል​ት​ንና ሌሊ​ት​ንም እን​ዲ​መ​ግቡ፥ በመ​ዓ​ል​ትና በሌ​ሊ​ትም መካ​ከል እን​ዲ​ለዩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። 19ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ አራ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።
20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ውኃ የሕ​ይ​ወት እስ​ት​ን​ፋስ ያላ​ቸ​ውን ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችና በም​ድር ላይ ከሰ​ማይ በታች የሚ​በ​ርሩ#ዕብ. “አዕ​ዋ​ፍም ይብ​ረሩ” ይላል። አዕ​ዋ​ፍን ታስ​ገኝ፥” እን​ዲ​ሁም ሆነ። 21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታላ​ላቅ አን​በ​ሪ​ዎ​ችን፥ ውኃ ያስ​ገ​ኘ​ውን ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ ሕያው ፍጥ​ረ​ትን ሁሉ በየ​ወ​ገኑ፥ የሚ​በ​ርሩ አዕ​ዋ​ፍ​ንም ሁሉ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ፈጠረ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። 22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ብሎ ባረ​ካ​ቸው፥ “ብዙ፤ ተባ​ዙም፤ የባ​ሕ​ር​ንም ውኃ ሙሉ​አት፤ ወፎ​ችም በም​ድር ላይ ይብዙ።” 23ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ አም​ስ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።
24እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ምድር ሕያ​ዋን ፍጥ​ረ​ታ​ትን እንደ ወገኑ፥ እን​ስ​ሳ​ት​ንና ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችን፥ የም​ድር አራ​ዊ​ት​ንም እን​ደ​የ​ወ​ገኑ ታውጣ፥” እን​ዲ​ሁም ሆነ። 25እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የም​ድር አራ​ዊ​ትን እን​ደ​የ​ወ​ገኑ፥ እን​ስ​ሳ​ት​ንም እን​ደ​የ​ወ​ገኑ፥ በም​ድር የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰ​ው​ንም ሁሉ እን​ደ​የ​ወ​ገኑ አደ​ረገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ።
26እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ሰውን በአ​ር​ኣ​ያ​ች​ንና በአ​ም​ሳ​ላ​ችን እን​ፍ​ጠር፤ የባ​ሕር ዓሣ​ዎ​ች​ንና የም​ድር አራ​ዊ​ትን፥#“አራ​ዊ​ትን” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። የሰ​ማይ ወፎ​ችን፥ እን​ስ​ሳ​ት​ንና ምድ​ርን ሁሉ፥ በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ትን ሁሉ ይግዛ።” 27እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ሳል ፈጠ​ረው። ወን​ድና ሴት አድ​ርጎ ፈጠ​ራ​ቸው። 28እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባረ​ካ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥#ዕብ. “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አላ​ቸው” ይላል። “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት፤ ግዙ​አ​ትም፤ የባ​ሕ​ርን ዓሣ​ዎ​ች​ንና የም​ድር አራ​ዊ​ትን፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “አራ​ዊ​ትን” አይ​ጽ​ፍም። የሰ​ማይ ወፎ​ች​ንና እን​ስ​ሳ​ት​ንም ሁሉ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ት​ንም ሁሉ ግዙ​አ​ቸው።”
29እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “እነሆ፥ መብል ይሆ​ና​ችሁ ዘንድ በየ​ዘሩ የሚ​ዘ​ራ​ው​ንና የሚ​በ​ቅ​ለ​ውን፥ በም​ድር ሁሉ ላይ የም​ት​ዘ​ሩ​ትን የእ​ህል ፍሬ፥ ዘሩ በው​ስጡ ያለ​ውን ቡቃያ፥ በየ​ፍ​ሬ​ውም የሚ​ዘ​ራ​ውን ዛፍ ሁሉ ሰጠ​ኋ​ችሁ። 30ለም​ድር አራ​ዊት ሁሉ፥ ለሰ​ማ​ይም ወፎች ሁሉ፥ ሕያው ነፍስ ላላ​ቸው ለም​ድር ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችም ሁሉ ሐመ​ል​ማሉ ሁሉ መብል ይሁ​ን​ላ​ችሁ።” እን​ዲ​ሁም ሆነ። 31እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፈ​ጠ​ረ​ውን ሁሉ እጅግ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ ስድ​ስ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

YouVersion uses cookies to personalize your experience. By using our website, you accept our use of cookies as described in our Privacy Policy