YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 3

3
1ከልጁ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸ ጊዜ የዳዊት መዝሙር።
2አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ!
በኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው።
3 # መዝ. 71፥11። ብዙ ሰዎች ነፍሴን፦
አምላክሽ አያድንሽም አልዋት።
4 # መዝ. 7፥11፤ 18፥3፤ 62፥7-8፤ ዘዳ. 33፥29፤ ኢሳ. 60፥19። አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ጋሻዬ ነህ፥
ክብሬና ራሴንም ቀና የምታደርገው አንተ ነህ።
5በሙሉ ድምጽ ወደ ጌታ እጮሃለሁ፥
ከተቀደሰ ተራራውም ይሰማኛል።
6 # መዝ. 4፥9፤ ምሳ. 3፥24። እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፥
ጌታም ደግፎኛልና ነቃሁ።
7የሚከቡኝን አእላፍ ሕዝብ አልፈራም።
8 # መዝ. 58፥7። ተነሥ፥ አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፥
አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና፥
የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና።
9 # መዝ. 28፥9፤ ዮናስ 2፥10። ማዳን የጌታ ነው፥
በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መዝሙረ ዳዊት 3