YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 12

12
1ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ስምንተኛው፥ የዳዊት መዝሙር።
2 # መዝ. 14፥3፤ 116፥11፤ ኢሳ. 59፥15፤ ሚክ. 7፥2። አቤቱ፥ አድነኝ፥ ደግ ሰው አልቆአልና፥
ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና።
3 # መዝ. 28፥3፤ 55፥22፤ ኢሳ. 59፥3-4፤ ኤር. 9፥7። እርስ በርሳቸው ከንቱ ነገርን ይናገራሉ፥
በሽንገላ ከንፈር ሁለት ልብ ሆነው ይናገራሉ።
4የሽንገላን ከንፈሮች ሁሉ ጌታ ያጠፋቸዋል፥
የትዕቢት ነገርን የምትናገረውን ምላስ
5 # ሲራ. 5፥3። ምላሳችንን እናበረታለን፥
ከንፈራችን የእኛ ነው፥ ጌታችን ማን ነው? የሚሉትን።
6 # ኢሳ. 33፥10። ስለ ምስኪኖች መከራ፥ ስለ ችግረኞች ጩኸት
ጌታ፦ አሁን እነሣለሁ ይላል፥
የተጠሙትንም ደኅንነት አመጣላቸዋለሁ።
7 # መዝ. 18፥31፤ 19፥8፤ ምሳ. 30፥5። በምድር ምድጃ ላይ እንደ ተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ ብር
የጌታ ቃላት የነጹ ቃላት ናቸው።
8አቤቱ፥ አንተ ጠብቀን፥
ከዚህችም ትውልድ ለዘለዓለም ታደገን።
9በሰው ልጆች ዘንድ ከንቱነት ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ
ክፉዎች በዙሪያው ሁሉ ይመላለሳሉ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in