YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 11

11
1ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
# መዝ. 55፥7፤ 91፥4። በጌታ ታመንሁ፥
ነፍሴን፦ እንዴት እንደ ወፍ ወደ ተራሮች ሽሺ ትሉአታላችሁ?
2 # መዝ. 7፥13፤ 37፥14፤ 57፥5፤ 64፥4። እነሆ ክፉዎች ቀስታቸውን ገትረዋልና፥
ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋልና፥
ልበ ቅኖችን በስውር ይነድፉ ዘንድ።
3መሠረቶቹ ከፈረሱ፥
ጻድቅ ምን ማድረግ ይችላል?
4 # መዝ. 14፥2፤ 102፥20፤ ዕን. 2፥20፤ ዘዳ. 26፥15፤ ኢሳ. 66፥1፤ ማቴ. 5፥34። ጌታ በተቀደሰው መቅደሱ ነው፥
ጌታ፥ ዙፋኑ በሰማይ ነው፥
ዐይኖቹ ይመለከታሉ፥
ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።
5ጌታ ጻድቅንና ክፉን ይመረምራል፥
ዓመፃ የሚወደውን ግን ነፍሱ ትጠላለች።
6 # መዝ. 120፥4፤ 140፥11፤ ምሳ. 16፥27፤ ሕዝ. 38፥22፤ ራእ. 8፥5፤ 20፥10። በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምንና ዲንን ያዘንባል
የሚያቃጥል ነፋስም የጽዋቸው እድል ፈንታ ነው።
7ጌታ ጻድቅ ነውና፥ ጽድቅንም ይወድዳል፥
ቅን ሰው ፊቱን ያየዋል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in