YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 83

83
የእስራኤል ጠላቶች እንዲሸነፉ የቀረበ ጸሎት
1አምላክ ሆይ! እባክህ ዝም አትበል፤
አትተወን፤ ችላ አትበል!
2እነሆ፥ ጠላቶችህ ዐምፀዋል፤
የሚጠሉህ ሁሉ ራሳቸውን በአንተ ላይ አንሥተዋል።
3በሕዝብህ ላይ በስውር ያደባሉ፤
አንተ በምትጠብቃቸው ላይ ያሤራሉ።
4“እስራኤል ለዘለዓለም የተረሳ እንዲሆን
ኑ፤ መንግሥታቸውን እንደምስስ” ይላሉ።
5በአንድነት በአንተ ላይ አሤሩ፤
በአንተ ላይ ለመነሣት የቃል ኪዳን ስምምነት አደረጉ።
6እነርሱም የኤዶም፥ የእስማኤል፥ የሞአብ፥ የአጋርያን፥
7የጌባል፥ የዐሞን፥ የዐማሌቅ፥ የፍልስጥኤምና የጢሮስ ሰዎች ናቸው።
8አሦርም የሎጥን ልጆች በመርዳት ከእነርሱ ጋር ተባብራለች።
9በምድያማውያን፥ በሲሣራና በያቢንም ላይ
በቂሾን ወንዝ ያደረግኸውን በእነዚህም ላይ አድርግ። #መሳ. 4፥6-22፤ 7፥1-23።
10እነርሱን በዔንዶር ድል አደረግሃቸው፤
ሬሳቸውም በሜዳ ላይ በስብሶ ቀረ።
11በዖሬብና በዜብ ላይ ያደረግኸውን
በእነርሱም መሪዎች ላይ አድርግ፤
በዜባሕና በጻልሙናዕ ያደረግኸውን
በእነርሱም ገዢዎች ላይ አድርግ። #መሳ. 7፥25፤ 8፥12።
12እነርሱ “የእግዚአብሔርን ሕዝብ ርስት የራሳችን
እናደርጋለን” ብለው ነበር።
13ስለዚህ አምላኬ ሆይ! እንደ ትቢያ፥
በነፋስም እንደሚወሰድ ገለባ በትናቸው።
14እሳት ደንን እንደሚያጋይ፥
የእሳት ነበልባልም ተራራዎችን እንደሚያቃጥል
15በሞገድህ አባራቸው፤
በዐውሎ ነፋስህም አስደንግጣቸው።
16እግዚአብሔር ሆይ! አንተን ይሹ ዘንድ
ፊታቸውን በኀፍረት ሸፍን፤
17ዐፍረው ለዘለዓለም ተስፋ እንዲቈርጡ አድርግ፤
ተዋርደውም እንዲጠፉ አድርግ።
18በምድር ሁሉ ላይ ጌታና ሁሉን ቻይ አምላክ
አንተ እግዚአብሔር እንደ ሆንክ ይወቁ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in