YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 82

82
እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ነው
1እግዚአብሔር በሰማያዊው ጉባኤ
አማልክት ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜ፥
በመካከላቸው ተገኝቶ ፍርድ ይሰጣል፦
2“እስከ መቼ ትክክል ያልሆነ ፍርድ ትፈርዳላችሁ?
እስከ መቼ ለክፉዎች ታዳላላችሁ?
3ለደካሞችና ለሙት ልጆች በትክክል ፍረዱ፤
የድኾችንና የተጨቈኑትን ሰዎች መብት ጠብቁ።
4ደካሞችንና ችግረኞችን አድኑ፤
ከክፉዎችም ጥቃት አስጥሉአቸው።
5“እነርሱ ግን ምንም አያውቁም፤ አይገባቸውምም፤
በጨለማ ይመላለሳሉ፤
በዚህም ጊዜ የምድር መሠረትዋ እየተናወጠ ነው።
6‘እናንተ አማልክት ናችሁ፤
ሁላችሁም የልዑል እግዚአብሔር ልጆች ናችሁ’ አልኩ። #ዮሐ. 10፥34።
7ነገር ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፤
የሕይወታችሁም ፍጻሜ እንደ ማንኛውም ምድራዊ ገዢ ነው።”
8አምላክ ሆይ! ተነሥ!
መንግሥታት ሁሉ ያንተ ስለ ሆኑ
ለዓለም ፍርድን ስጥ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in