YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 131

131
በእግዚአብሔር መታመን
1እግዚአብሔር ሆይ! ልቤ በኩራት የተወጠረ አይደለም፤
ዐይኖቼም ትዕቢተኞች አይደሉም፤
ስለ ታላላቅ ነገሮች ወይም ላስተውለው
ስለማልችለው ከባድ ነገር አልጨነቅም።
2አንድ ጡት የተወ ሕፃን በእናቱ ደረት ላይ እንደሚለጠፍ
እኔም ዝምተኛና ጸጥተኛ ሆንኩ።
3እስራኤል ሆይ! ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም
እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ!

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for መጽሐፈ መዝሙር 131