መጽሐፈ መዝሙር 129
129
ከእስራኤል ጠላቶች ለመዳን የቀረበ መዝሙር
1ከወጣትነቴ ጀምሮ አደጋ ደርሶብኛል፤
እስራኤላውያን እንዲህ ይበሉ፦
2“ከወጣትነቴ ጀምሮ ጠላቶቼ
በጭካኔ አሳደዱኝ፤
ነገር ግን አላሸነፉኝም።
3ጀርባዬን በጅራፍ ተልትለው፥
የታረሰ ማሳ አስመስለውታል።
4እግዚአብሔር ሁልጊዜ ትክክለኛ ነው፤
ከእነዚያ ጨካኞች ገመድ ነጻ አውጥቶኛል።”
5ጽዮንን የሚጠላ ሁሉ ይሸነፍ!
ወደ ኋላውም ይመለስ!
6በቤት ጣራ ላይ እንደሚበቅልና
ከማደጉ በፊት እንደሚደርቅ ሣር ይሁን።
7እንዲህ ዐይነቱን ሣር ማንም አይሰበስበውም፤
ወይም ነዶው በእጁ አይሞላም።
8በአጠገባቸው የሚያልፉት ሁሉ ለጽዮን ጠላቶች
“እግዚአብሔር ይባርካችሁ!
እኛም በእግዚአብሔር ስም እንባርካችኋለን!”
አይሉአቸውም።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 129: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997