YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ ኢያሱ መግቢያ

መግቢያ
መጽሐፈ ኢያሱ የእስራኤል ሕዝብ በሙሴ እግር ተተክቶ በተሾመው በኢያሱ መሪነት በጦርነት ድል ነሥተው ከነዓንን እንዴት እንደ ያዙ የሚገልጥ ታሪክ ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከተመዘገቡት ታላላቅ ታሪኮች መካከል ዋና ዋናዎቹ፦ የዮርዳኖስን ወንዝ ስለ መሻገር፥ ስለ ኢያሪኮ ግንብ መፍረስ፥ ዐይ በምትባለዋ ከተማ ስለ ተደረገው ጦርነትና ሕዝቡ ከእግዚአብሔር ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ስለ ማደሱ የሚናገሩት ናቸው። በመጽሐፉ ውስጥ በጣም ታዋቂ ከሆኑት ክፍሎች አንዱ “የምታመልኩትን ዛሬውኑ ምረጡ፤ እኔና ቤተሰቤ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን” (ም. 24፥15) የሚለው ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
የከነዓን ድል መሆን 1፥1—12፥24
የመሬት ክፍፍል 13፥1—21፥45
ሀ. ከዮርዳኖስ ምሥራቅ ያለው መሬት 13፥1-33
ለ. ከዮርዳኖስ ምዕራብ ያለው መሬት 14፥1—19፥51
ሐ. የመማጠኛ ከተሞች 20፥1-9
መ. የሌዋውያን ከተሞች 21፥1-45
ከምሥራቅ የመጡት ነገዶች ወደ ቦታቸው መመለስ 22፥1-34
የኢያሱ የመሰናበቻ ንግግር 23፥1-16
በሴኬም የቃል ኪዳኑ መታደስ 24፥1-33

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in