YouVersion Logo
Search Icon

ትንቢተ ሐጌ መግቢያ

መግቢያ
በትንቢተ ሐጌ የተጠናቀሩት አጫጭር መልእክቶች እግዚአብሔር ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስት መቶ ዓመት በነቢዩ ሐጌ አማካይነት ያስተላለፋቸው ናቸው። ሕዝቡ ከስደት ተመልሰው በኢየሩሳሌም መኖር ከጀመሩ ጥቂት ዓመቶች ያለፋቸው ቢሆንም እንኳ ቤተ መቅደሱ ገና እንደ ፈረሰ ነበር፤ ስለዚህ መልእክቱ የሕዝቡ መሪዎች ቤተ መቅደሱን እንዲያድሱ የሚገፋፋ ነበር፤ ሕዝቡ ተሐድሶና ንጽሕና የሚኖራቸው ከሆነም፥ እግዚአብሔር ወደ ፊት ሰላምና ብልጽግና እንደሚሰጣቸው ይናገራል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
1. ጌታ ቤተ መቅደሱ እንዲሠራ ማዘዙ 1፥1-15
2. ጌታ ለሕዝቡ የሰጠው የበረከትና የማጽናናት ተስፋ 2፥1-19
3. እግዚአብሔር ዘሩባቤል የሰጠው ተስፋ 2፥20-23

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in