መዝሙር 6
6
መዝሙር 6
ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች የሚዘመር፤ የዳዊት መዝሙር በሸሚኒት#6 ርእሱ በሙዚቃ ውስጥ የሚጠቀሙበት ቃል ሳይሆን አይቀርም።።
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ በቍጣህ አትገሥጸኝ፤
በመዓትህም አትቅጣኝ።
2 እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐቅመ ቢስ ነኝና ማረኝ፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐጥንቶቼ ተናግተዋልና ፈውሰኝ።
3ነፍሴ እጅግ ታውካለች፤
እስከ መቼ፣ አንተ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ድረስ ይሆናል?
4 እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስና ሕይወቴን ታደጋት፤
ስለ ጽኑ ፍቅርህም አድነኝ፤
5በሞት የሚያስታውስህ የለምና፤
በሲኦልስ#6፥5 ወይም በመቃብር ማን ያመሰግንሃል?
6ከመቃተቴ የተነሣ ዝያለሁ።
ሌሊቱን ሁሉ በልቅሶ ዐልጋዬን አርሳለሁ፤
መኝታዬንም በእንባዬ አሾቃለሁ።
7ዐይኖቼ በሐዘን ብዛት ደክመዋል፤
ከጠላቶቼም ሁሉ የተነሣ ማየት ተስኗቸዋል።
8እናንተ ክፉ አድራጊዎች ሁሉ፤ ከእኔ ራቁ፤
እግዚአብሔር የልቅሶዬን ድምፅ ሰምቷልና።
9 እግዚአብሔር ልመናዬን ሰምቷል፤
እግዚአብሔር ጸሎቴን ይቀበላል።
10ጠላቶቼ ሁሉ ያፍራሉ፤ እጅግም ይደነግጣሉ፤
በመጡበት ይመለሳሉ፤ ድንገትም ይዋረዳሉ።
Currently Selected:
መዝሙር 6: NASV
Highlight
Share
Copy

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.