YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙር 146

146
መዝሙር 146
1ሃሌ ሉያ።#146፥1 አንዳንዶች ከቍጥር 10 ጭምር እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ።
ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ።
2በምኖርበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን
አመሰግናለሁ፤
በሕይወትም እስካለሁ ለአምላኬ እዘምራለሁ።
3በገዦች አትታመኑ፤ ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችም አትመኩ።
4መንፈሳቸው ትወጣለች፤ ወደ መሬታቸውም ይመለሳሉ፤
ያን ጊዜም ዕቅዳቸው እንዳልነበር ይሆናል።
5ብፁዕ ነው፤
ረዳቱ የያዕቆብ አምላክ የሆነ፣
ተስፋውንም በአምላኩ በእግዚአብሔር ላይ የጣለ ሰው፤
6እርሱ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንም፣
በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ የፈጠረ፣
ታማኝነቱም ለዘላለም የሆነ ነው፤
7ለተበደሉት የሚፈርድ፣
ለተራቡት ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፤
እግዚአብሔር እስረኞችን ከእስራት ያወጣል፤
8 እግዚአብሔር የዕውራንን ዐይን ያበራል፤
እግዚአብሔር የተዋረዱትን ከፍ ያደርጋል፤
እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤
9 እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል፤
ድኻ አደጎችንና መበለቶችን ይደግፋል፤
የክፉዎችን መንገድ ግን ያጠፋል።
10 እግዚአብሔር ለዘላለም ይነግሣል፤
ጽዮን ሆይ፤ አምላክሽ ለትውልድ ሁሉ ንጉሥ ነው።
ሃሌ ሉያ።

Currently Selected:

መዝሙር 146: NASV

Highlight

Share

Compare

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in