YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙር 101

101
መዝሙር 101
የዳዊት መዝሙር።
1ስለ ምሕረትና ስለ ፍትሕ እዘምራለሁ፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ ለአንተ በምስጋና እቀኛለሁ።
2እንከን የማይገኝባትን መንገድ አጥብቄ እይዛለሁ፤
አንተ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ነው?
በቤቴ ውስጥ፣
በንጹሕ ልብ እመላለሳለሁ።
3በዐይኔ ፊት፣
ምናምንቴ ነገር አላኖርም።
የከሓዲዎችን ሥራ እጠላለሁ፤
ከእኔም ጋራ አይጣበቅም።
4ጠማማ ልብ ከእኔ ይርቃል፤
ለክፋትም ዕውቅና አልሰጥም።
5ባልንጀራውን በስውር የሚያማውን፣
አጠፋዋለሁ፤
ትዕቢተኛ ዐይንና ኵራተኛ ልብ ያለውን፣
እርሱን አልታገሠውም።
6ከእኔ ጋራ ይኖሩ ዘንድ፣
ዐይኖቼ በምድሪቱ ታማኞች ላይ ናቸው፤
በፍጹም መንገድ የሚሄድ፣
እርሱ ያገለግለኛል።
7አታላይ የሆነ ማንም ሰው፣
በቤቴ ውስጥ አይኖርም፤
ሐሰትን የሚናገር፣
በፊቴ ቀና ብሎ አይቆምም።
8በምድሪቱ ላይ ያሉትን ክፉዎች ሁሉ፣
በየማለዳው አጠፋቸዋለሁ፤
ክፉ አድራጊዎችንም ሁሉ፣
እግዚአብሔር ከተማ እደመስሳቸዋለሁ።

Currently Selected:

መዝሙር 101: NASV

Highlight

Copy

Compare

Share

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for መዝሙር 101