YouVersion Logo
Search Icon

ዮናስ 2

2
የዮናስ ጸሎት
1ዮናስ በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ 2እንዲህም አለ፤
“ተጨንቄ ሳለሁ ወደ እግዚአብሔር ተጣራሁ፤
እርሱም መለሰልኝ፤
ከመቃብሩም#2፥2 የዕብራይስጡ ትርጕም ሲዖል ይላል። ጥልቅ ርዳታን ፈልጌ ተጣራሁ፤
አንተም ጩኸቴን ሰማህ።
3ጥልቅ ወደ ሆነው፣
ወደ ባሕሩ መካከል ጣልኸኝ፤
ፈሳሾችም ዙሪያዬን ከበቡኝ፤
ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ፣
በላዬ ዐለፉ።
4እኔም፣ ‘ከፊትህ ጠፋሁ፣
ነገር ግን እንደ ገና፣
ወደ ቅዱስ መቅደስህ፣
እመለከታለሁ’ አልሁ።
5ውሃ እስከ ዐንገቴ አጠለቀኝ#2፥5 ወይም “ውሃ ከብቦ አስፈራራኝ”
ጥልቁም ከበበኝ፤
የባሕርም ዐረም በራሴ ላይ ተጠመጠመ።
6ወደ ተራሮች መሠረት ሰመጥሁ፤
የምድርም በር ለዘላለም ተዘጋብኝ፤
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤
አንተ ግን ሕይወቴን ከጕድጓድ አወጣህ።
7“ነፍሴ በዛለች ጊዜ፣
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን ዐሰብሁ፤
ጸሎቴም ወደ አንተ፣
ወደ ቅዱስ መቅደስህ ዐረገች።
8“ከንቱ በሆኑ ጣዖቶች ላይ የሚንጠለጠሉ፣
ሊያገኙ የሚገባቸውን ጸጋ ያጣሉ።
9እኔ ግን በምስጋና መዝሙር፣
መሥዋዕት እሠዋልሃለሁ፤
የተሳልሁትንም እሰጣለሁ፤
ድነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።”
10 እግዚአብሔርም ዓሣውን አዘዘው፤ ዮናስንም በደረቅ ምድር ላይ ተፋው።

Currently Selected:

ዮናስ 2: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

YouVersion uses cookies to personalize your experience. By using our website, you accept our use of cookies as described in our Privacy Policy