ኢዮብ 35
35
1ኤሊሁ ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤
2“ ‘በእግዚአብሔር ፊት ንጹሕ ነኝ’#35፥2 ወይም፣ ጽድቄ ከእግዚአብሔር ጽድቅ ይበልጣል ማለትህ፣
ትክክል ይመስልሃልን?
3ደግሞ ‘ያገኘሁት#35፥3 ወይም፣ ያገኘኸው ጥቅም ምንድን ነው?
ኀጢአት ባለመሥራቴስ ምን አተረፍሁ?’ ብለህ ጠይቀኸዋል።
4“ለአንተና ዐብረውህ ላሉት ባልንጀሮችህ፣
መልስ መስጠት እፈልጋለሁ።
5ቀና ብለህ ወደ ሰማይ እይ፤
ከአንተ በላይ ከፍ ብለው ያሉትንም ደመናት ተመልከት።
6ኀጢአትህስ ቢበዛ እርሱን ምን ትጐዳዋለህ?
ኀጢአትህስ ቢበዛ ምን ያደርገዋል?
7ጻድቅ ብትሆንም ለርሱ ምን ትሰጠዋለህ?
ከእጅህስ ምን ይቀበላል?
8ክፋትህ የሚጐዳው እንደ አንተ ያለውን ሰው ብቻ ነው፤
ጽድቅህም የሚጠቅመው የሰውን ልጆች ብቻ ነው።
9“ሰው ከጭቈና ብዛት የተነሣ ይጮኻል፤
ከኀያሉም ክንድ ሥር ለመውጣት ለርዳታ ይጣራል።
10ነገር ግን እንዲህ የሚል የለም፤ ‘ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ወዴት ነው?
በሌሊት መዝሙርን የሚሰጥ፣
11ከምድር እንስሳት ይልቅ የሚያስተምረን፣
ከሰማይ ወፎችም ይልቅ ጠቢባን የሚያደርገን፣ እርሱ የት አለ?’
12ከዐመፀኞች ትዕቢት የተነሣ፣
ሰዎች ሲጮኹ አይመልስላቸውም፤
13በርግጥ እግዚአብሔር ከንቱ ጩኸታቸውን አይሰማም፤
ሁሉን ቻይ አምላክ አያዳምጣቸውም።
14ጕዳይህን ፊቱ አቅርበህ፣
ብዙ ጠብቀኸው፣
ግን እንዳላየኸው ስትናገር፣
ታዲያ፣ አንተን እንዴት ይስማህ!
15ደግሞም፣ ቍጣው ቅጣት እንደማያስከትል፣
ኀጢአትንም#35፥15 ሴማኮስ፣ ቴዎዴሽንና ቩልጌት ከዚህ ጋራ ይስማማል፤ ነገር ግን በዕብራይስጡ የዚህ ቃል ትርጕም አይታወቅም ከቍጥር እንደማያስገባ ተናግረሃል።
16ስለዚህ ኢዮብ አፉን በከንቱ ይከፍታል፤
ዕውቀት አልባ ቃላትም ያበዛል።”
Currently Selected:
ኢዮብ 35: NASV
Highlight
Share
Copy

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.