YouVersion Logo
Search Icon

ሆሴዕ 14

14
በረከትን ለማግኘት ንስሓ መግባት
1እስራኤል ሆይ፤ በኀጢአትህ ምክንያት ስለ ወደቅህ፣
ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ።
2የምትሉትን ቃል ይዛችሁ፣
ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤
እንዲህም በሉት፤
“ኀጢአታችንን ሁሉ ይቅር በለን፤
የከንፈራችንንም ፍሬ እንድናቀርብ፣#14፥2 ወይም እንደ ኮርማዎች መሥዋዕት የከንፈራችንን ፍሬ እንድናቀርብ
በምሕረትህ ተቀበለን።
3አሦር ሊያድነን አይችልም፤
በጦር ፈረሶችም ላይ አንቀመጥም፤
ከእንግዲህም የገዛ እጆቻችን የሠሯቸውን፣
‘አምላኮቻችን’ አንላቸውም፤
ድኻ ዐደጉ ከአንተ ርኅራኄ ያገኛልና።”
4“እኔ ከዳተኛነታቸውን እፈውሳለሁ፤
እንዲሁ እወድዳቸዋለሁ፤
ቍጣዬ ከእነርሱ ተመልሷልና።
5እኔ ለእስራኤል እንደ ጠል እሆናለሁ፤
እንደ ውብ አበባ ያብባል፤
እንደ ሊባኖስ ዝግባም፣
ሥር ይሰድዳል፤
6ቅርንጫፉ ያድጋል፤
ውበቱ እንደ ወይራ ዛፍ፣
ሽታውም እንደ ሊባኖስ ዝግባ ይሆናል።
7ሰዎች እንደ ገና ከጥላው በታች ያርፋሉ፤
እርሱም እንደ እህል ይለመልማል፤
እንደ ወይን ተክል ያብባል፤
ዝናውም እንደ ሊባኖስ የወይን ጠጅ ይወጣል።
8ኤፍሬም ሆይ፤ ከእንግዲህ ከጣዖት ጋር
ምን ጕዳይ አለኝ?#14፥8 ወይም ከእንግዲህ ከጣዖት ጋር ኤፍሬም ሌላ ምን አለው?
የምሰማህና የምጠነቀቅልህ እኔ ነኝ፤
እኔ እንደ ለመለመ የጥድ ዛፍ ነኝ፤
ፍሬያማነትህም ከእኔ የተነሣ ነው።”
9ጥበበኛ የሆነ እነዚህን ነገሮች ያስተውላል፤
አስተዋይም እነዚህን ነገሮች ይረዳል።
የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ነውና፤
ጻድቃን ይሄዱበታል፤
ዐመፀኞች ግን ይሰናከሉበታል።

Currently Selected:

ሆሴዕ 14: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

YouVersion uses cookies to personalize your experience. By using our website, you accept our use of cookies as described in our Privacy Policy