YouVersion Logo
Search Icon

ዕዝራ 2

2
ወደ አገራቸው የተመለሱ ምርኮኞች ዝርዝር
2፥1-70 ተጓ ምብ – ነህ 7፥6-73
1የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ማርኮ ከወሰዳቸው መካከል ከምርኮ ተመልሰው ወደ የራሳቸው ከተሞች፣ ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም የመጡት የአገሩ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ 2የመጡትም ከዘሩባቤል፣ ከኢያሱ፣ ከነህምያ፣ ከሠራያ፣ ከረዕላያ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከበላሳን፣ ከመሴፋር፣ ከበጉዋይ፣ ከሬሁም፣ ከበዓና ጋር ነበር።
የተመለሱት የእስራኤል ሰዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው፦
3የፋሮስ ዘሮች 2,172
4የሰፋጥያስ ዘሮች 372
5የኤራ ዘሮች 775
6ከኢያሱና ከኢዮአብ ዘር የሆኑት የፈሐት ሞዓብ ዘሮች 2,812
7የኤላም ዘሮች 1,254
8የዛቱዕ ዘሮች 945
9የዘካይ ዘሮች 760
10የባኒ ዘሮች 642
11የቤባይ ዘሮች 623
12የዓዝጋድ ዘሮች 1,222
13የአዶኒቃም ዘሮች 666
14የበጉዋይ ዘሮች 2,056
15የዓዲን ዘሮች 454
16የሕዝቅያስ ልጅ የአጤር ዘሮች 98
17የቤሳይ ዘሮች 323
18የዮራ ዘሮች 112
19የሐሱም ዘሮች 223
20የጋቤር ዘሮች 95
21የቤተ ልሔም ሰዎች#2፥21 ወይም ልጆች፣ ዘሮች 123
22የነጦፋ ሰዎች 56
23የዓናቶት ሰዎች 128
24የዓዝሞት ዘሮች 42
25የቂርያትይዓሪም#2፥25 የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም (እንዲሁም ነህ 7፥29 ይመ)፤ ዕብራይስጡ ግን፣ ቂሪያት ኦሪም ይላል።፣ የከፊራና የብኤሮት ዘሮች 743
26የራማና የጌባ ዘሮች 621
27የማክማስ ሰዎች 122
28የቤቴልና የጋይ ሰዎች 223
29የናባው ዘሮች 52
30የመጌብስ ዘሮች 156
31የሌላው ኤላም ዘሮች 1,254
32የካሪም ዘሮች 320
33የሎድ፣ የሐዲድና 725
34የኢያሪኮ ሰዎች 345
35የሴናዓ ዘሮች 3,630
36ካህናቱ፦
ከኢያሱ ቤተ ሰብ የዮዳኤ ዘሮች 973
37የኢሜር ዘሮች 1,052
38የፋስኮር ዘሮች 1,247
39የካሪም ዘሮች 1,017
40ሌዋውያኑ፦
በሆዳይዋ በኩል የኢያሱና የቀድምኤል ዘሮች 74
41መዘምራኑ፦
የአሳፍ ዘሮች 128
42የቤተ መቅደሱ በረኞች፦
የሰሎም፣ የአጤር፣ የጤልሞን፣ የዓቁብ፣ የሐጢጣና የሶባይ ዘሮች 139
43የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፦
የሲሐ፣ የሐሡፋና የጠብዖት ዘሮች፤
44የኬራስ፣ የሲዓ፣ የፋዶን ዘሮች፤
45የልባና፣ የአጋባ፣ የዓቁብ ዘሮች፤
46የአጋብ፣ የሰምላይ፣ የሐናን ዘሮች፤
47የጌዴል፣ የጋሐር፣ የራያ ዘሮች፤
48የረአሶን፣ የኔቆዳ፣ የጋሴም ዘሮች፤
49የዖዛ፣ የፋሴሐ፣ የቤሳይ ዘሮች፤
50የአስና፣ የምዑናውያን፣ የንፉሰሲም ዘሮች፤
51የበቅቡቅ፣ የሐቁፋ፣ የሐርሑር ዘሮች፤
52የበስሎት፣ የምሒዳ፣ የሐርሳ ዘሮች፤
53የበርቆስ፣ የሲሣራ፣ የቴማ ዘሮች፤
54የንስያና የሐጢፋ ዘሮች።
55የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች፦
የሶጣይ፣ የሶፌሬት፣ የፍሩዳ ዘሮች፤
56የየዕላ፣ የደርቆን፣ የጌዴል ዘሮች፤
57የሰፋጥያስ፣ የሐጢል፣
የፈክራት ሐፂቦይም፣ የአሚ ዘሮች፤
58የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች 392
59ከዚህ የሚከተሉት ደግሞ ከቴልሜላ፣ ከቴላሬሳ፣ ከክሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር ከተሞች የመጡ ናቸው፤ ነገር ግን ቤተ ሰቦቻቸው የእስራኤል ዘር መሆናቸውን ማስረዳት አልቻሉም፦
60የዳላያ፣ የጦብያና የኔቆዳ ዘሮች 652
61ከካህናቱ መካከል፦
የኤብያ፣ የአቆስና የቤርዜሊ ዘሮች፤ ቤርዜሊ በዚህ ስም ሊጠራ የቻለው የገለዓዳዊውን የቤርዜሊን ልጅ አግብቶ ስለ ነበር ነው።
62እነዚህ በትውልድ መዝገቡ ውስጥ የቤተ ሰባቸውን ዝርዝር ፈለጉ፤ ነገር ግን ማግኘት አልቻሉም፤ ስለዚህ እንዳልነጹ ተቈጥረው፣ ከክህነት አገልግሎት ተገለሉ። 63አገረ ገዥውም በኡሪምና በቱሚም እግዚአብሔርን የሚጠይቅ ካህን እስኪነሣ ድረስ፣ እጅግ ከተቀደሰው ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው።
64ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ብዛት 42,360 ነበረ፤ 65ይህም 7,337 ከሚሆኑት ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻቸው በተጨማሪ ነው፤ 200 ወንድና ሴት ዘማሪዎችም ነበሯቸው። 66736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች፣ 67435 ግመሎችና 6,720 አህዮች ነበሯቸው።
68በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት በደረሱ ጊዜ፣ አንዳንድ የቤተ ሰብ መሪዎች በቀድሞው ቦታ እንደ ገና ለሚሠራው የእግዚአብሔር ቤት በበጎ ፈቃድ ስጦታ አደረጉ። 69እንደየችሎታቸውም 61,000 የወርቅ ዳሪክ#2፥69 500 ኪሎ ግራም ያህል ነው።፣ 5,000 ምናን#2፥69 2.9 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው። ብር፣ 100 ልብሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጡ።
70ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ መዘምራኑ፣ በር ጠባቂዎቹና የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ፤ የቀሩት እስራኤላውያንም በየከተሞቻቸው ተቀመጡ።

Currently Selected:

ዕዝራ 2: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

YouVersion uses cookies to personalize your experience. By using our website, you accept our use of cookies as described in our Privacy Policy