YouVersion Logo
Search Icon

አስቴር 10

10
የመርዶክዮስ ታላቅነት
1ንጉሥ ጠረክሲስ እስከ ባሕር ዳርቻ በሚዘልቀው ግዛቱ ሁሉ ላይ ግብር ጣለ። 2የኀይሉና የብርታቱ ሥራ ሁሉ እንዲሁም ንጉሡ መርዶክዮስን ለዚህ የላቀ ማዕርግ እንዴት እንዳደረሰው የሚናገረው በሜዶንና በፋርስ የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? 3አይሁዳዊው መርዶክዮስ በማዕርግ ከንጉሡ ከጠረክሲስ ቀጥሎ ሁለተኛ፣ ከአይሁድ መካከልም ቀዳሚውን ስፍራ የያዘ ሰው ነበር፤ ለወገኖቹ መልካም በማድረጉና ለአይሁድም ሁሉ ደኅንነት የቆመ በመሆኑ፣ በብዙዎቹ አይሁድ ወገኖቹ ዘንድ እጅግ የተከበረ ነበር።

Currently Selected:

አስቴር 10: NASV

Highlight

Share

Compare

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in