YouVersion Logo
Search Icon

አሞጽ 2

2
1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ስለ ሦስቱ የሞዓብ ኀጢአት፣
ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤
የኤዶምን ንጉሥ ዐጥንት፣
ዐመድ እስኪሆን ድረስ አቃጥሏልና፤
2የቂርዮትን ምሽጎች#2፥2 ወይም ከተሞቿ እንዲበላ፣
በሞዓብ ላይ እሳት እሰድዳለሁ፤
ሞዓብ በጦርነት ጩኸትና በመለከት ድምፅ መሐል፣
በታላቅ ሁካታ ውስጥ ይሞታል።
3ገዧን እደመስሳለሁ፣
አለቆቿንም ሁሉ ከንጉሧ ጋር እገድላለሁ፤”
ይላል እግዚአብሔር
4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ስለ ሦስቱ የይሁዳ ኀጢአት፣
ይልቁን ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤
የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋል፤
ትእዛዙንም አልጠበቁምና፤
አባቶቻቸው በተከተሏቸው#2፥4 ወይም በውሸት አማልክት፣
በሐሰት#2፥4 ወይም ውሸት አማልክት በመመራት ስተዋልና።
5የኢየሩሳሌምን ምሽጎች እንዲበላ፣
በይሁዳ ላይ እሳት እሰድዳለሁ።”
በእስራኤል ላይ የተሰጠ ፍርድ
6 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ስለ ሦስቱ የእስራኤል ኀጢአት፣
ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤
ጻድቁን ስለ ጥሬ ብር፣
ችግረኛውንም ስለ ጥንድ ጫማ ይሸጡታልና።
7የድኾችን ራስ፣
በምድር ትቢያ ላይ ይረግጣሉ፤
ፍትሕንም ከጭቍኖች ይነጥቃሉ፤
አባትና ልጅ ከአንዲት ሴት ጋር ይተኛሉ፤
እንዲህም እያደረጉ ቅዱስ ስሜን ያረክሳሉ።
8በመያዣነት በተወሰደው ልብስ ላይ፣
በየመሠዊያው ሥር ይተኛሉ፤
በአምላካቸው ቤት፣
በመቀጫነት የተወሰደውን የወይን ጠጅ ይጠጣሉ።
9“ቁመቱ እንደ ዝግባ፣
ጥንካሬውም እንደ ባሉጥ ዛፍ የነበረ ቢሆንም፣
አሞራዊውን ከፊታቸው አጠፋሁት፣
ከላይ ፍሬውን፣
ከታችም ሥሩን አጠፋሁ።
10የአሞራውያንን ምድር ልሰጣችሁ፣
ከግብፅ አወጣኋችሁ፤
አርባ ዓመትም በምድረ በዳ መራኋችሁ።
11“ደግሞም ነቢያትን ከወንዶች ልጆቻችሁ መካከል፣
ናዝራውያንንም ከጕልማሶቻችሁ መካከል አስነሣሁ፤
የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፤ ይህ እውነት አይደለምን?”
ይላል እግዚአብሔር
12“እናንተ ግን ናዝራውያኑን የወይን ጠጅ አጠጣችኋቸው፤
ነቢያቱንም ትንቢት እንዳይናገሩ አዘዛችኋቸው።
13“እነሆ፤ በእህል የተሞላ ጋሪ እንደሚያደቅቅ፣
እኔም አደቅቃችኋለሁ።
14ፈጣኑ አያመልጥም፤
ብርቱውንም ብርታቱ አይረዳውም፤
ኀያሉም ነፍሱን አያድንም።
15ቀስተኛው በቦታው ጸንቶ አይቆምም፤
ፈጣኑም ተዋጊ ሮጦ አያመልጥም፤
ፈረሰኛውም ነፍሱን አያድንም።
16ጐበዞቹ ተዋጊዎች እንኳ፣
በዚያ ቀን ዕራቁታቸውን ይሸሻሉ፤”
ይላል እግዚአብሔር

Currently Selected:

አሞጽ 2: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

YouVersion uses cookies to personalize your experience. By using our website, you accept our use of cookies as described in our Privacy Policy