YouVersion Logo
Search Icon

2 ሳሙኤል 22

22
የዳዊት የምስጋና መዝሙር
22፥1-51 ተጓ ምብ – መዝ 18፥1-50
1 እግዚአብሔር ከጠላቶቹ ሁሉና ከሳኦል እጅ በታደገው ጊዜ፣ ዳዊት የዚህን መዝሙር ቃል ለእግዚአብሔር ዘመረ፤ 2እንዲህም አለ፤
እግዚአብሔር ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፤
3አምላኬ፣ የምሸሸግበት ዐለቴ፣
ጋሻዬና የድነቴ ቀንድ#22፥3 ቀንድ የጥንካሬ ወይም የኀይል ምልክት ነው። ነው፤
እርሱም ጠንካራ ምሽጌ፣ መጠጊያና አዳኜ ነው፤
ከዐመፀኛ ሰዎችም ታድነኛለህ።
4“ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤
ከጠላቶቼም እድናለሁ።
5የሞት ማዕበል ከበበኝ፤
ምናምንቴ ነገርም አጥለቀለቀኝ።
6የሲኦል ገመድ ተጠመጠመብኝ፤
የሞት ወጥመድም ተጋረጠብኝ።
7“በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤
ወደ አምላኬም ጮኽሁ።
እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤
ጩኸቴም ከጆሮው ደረሰ።
8ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤
የሰማያትም መሠረቶች#22፥8 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋራ ይስማማል፤ ቩልጌትና ሱርስቱ ግን (እንዲሁም መዝ 18፥7 ይመ) ተራሮች ይላሉ። ተናጉ፤
እርሱ ተቈጥቷልና ተንቀጠቀጡ።
9ከአፍንጫው ጢስ ወጣ፤
ከአፉ የሚባላ እሳት ነደደ፤
ከውስጡም ፍሙ ጋለ።
10ሰማያትን ሰንጥቆ ወረደ፤
ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ።
11በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤
በነፋስም ክንፍ መጠቀ።#22፥11 አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች (እንዲሁም መዝ 18፥10 ይመ) ከዚህ ጋራ ይስማማሉ፤ እጅግ ብዙ የሆኑ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ ተገለጠ ይላሉ።
12ጨለማው በዙሪያው እንዲከብበው፣
ጥቅጥቅ ያለውም የሰማይ ዝናም ደመና እንዲሰውረው አደረገ።
13በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ፣
የመብረቅ ብልጭታ ወጣ።
14 እግዚአብሔር ከሰማያት አንጐደጐደ፤
የልዑልም ድምፅ አስተጋባ።
15ፍላጻውን ሰድዶ በተናቸው፤
ታላቅ መብረቆቹንም ልኮ አወካቸው።
16እግዚአብሔር ተግሣጽ፣ ከአፍንጫው ከሚወጣው፣
ከእስትንፋሱ ቍጣ የተነሣ፣
የባሕር ወለል ታየ፤
የምድር መሠረቶችም ተገለጡ።
17“ከላይ እጁን ዘርግቶ ያዘኝ፤
ከጥልቅ ውሆችም ውስጥ አወጣኝ።
18ከብርቱ ጠላቶቼ አዳነኝ፤
ከሚበረቱብኝ ባላጋሮቼም ታደገኝ።
19በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤
እግዚአብሔር ግን ድጋፍ ሆነኝ።
20ወደ ሰፊ ስፍራ አወጣኝ፤
ደስ ተሰኝቶብኛልና አዳነኝ።
21እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ መለሰልኝ፤
እንደ እጄም ንጽሕና ከፈለኝ፤
22እግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፤
አምላኬንም በመተው ክፉ አላደረግሁም።
23ሕጎቹ ሁሉ በፊቴ ናቸው፤
ከሥርዐቱም ዘወር አላልሁም።
24በፊቱ ነቀፋ አልነበረብኝም፤
ራሴንም ከኀጢአት ጠብቄአለሁ።
25 እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ፣
በፊቱም እንዳለኝ ንጽሕና#22፥25 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋራ ይስማማል፤ የሰብዓ ሊቃናትና የቩልጌት ትርጉሞች (እንዲሁም መዝ 18፥24 ይመ) ግን፣ እንደ እጄም ንጽሕና ይላሉ። ብድራትን ከፈለኝ።
26“ለታማኝ ሰው ታማኝ መሆንህን፣
ለፍጹም ሰው ፍጹም መሆንህን ታሳያለህ።
27ለንጹሕ ሰው አንተም ንጹሕ መሆንህን፣
ለጠማማ ሰው ግን አንተም ጠማማ መሆንህን ታሳያለህ።
28አንተ ትሑታንን ታድናለህ፤
ዐይንህ ግን ያዋርዳቸው ዘንድ፣ ትዕቢተኞችን ይመለከታል።
29 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ መብራቴ ነህ፤
እግዚአብሔርም ጨለማዬን ያበራል።
30በአንተ ጕልበት በሰራዊት ላይ እረማመዳለሁ#22፥30 ወይም በጋሬጣዎች ውስጥ እሮጣለሁ
በአምላኬም ኀይል ቅጥር እዘላለሁ።
31“የአምላክ መንገዱ ፍጹም ነው፤
እግዚአብሔርም ቃል የነጠረ ነው፤
መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻ ነው።
32እግዚአብሔር በቀር ማን አምላክ አለ?
ከአምላካችንስ በቀር ዐለት ማን ነው?
33ኀይልን የሚያስታጥቀኝ#22፥33 የሙት ባሕር ጥቅልል፣ አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች፣ የቩልጌትና የሱርስት ቅጆች (እንዲሁም መዝ 18፥32 ይመ) ከዚህ ጋራ ይስማማሉ፤ የማሶሬቱ ቅጅ ግን፣ ጠንካራ መሸሸጊያ የሚሆነኝ ይላል።
መንገዴንም የሚያቀና እርሱ አምላኬ ነው።
34እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች ያደርጋል፤
በከፍታዎችም ላይ አጽንቶ ያቆመኛል።
35እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናቸዋል፤
ክንዶቼም የናስ ቀስት መገተር ይችላሉ።
36የማዳንህን ጋሻ ሰጥተኸኛል፤
ድጋፍህ ታላቅ አድርጎኛል።
37ርምጃዬን አሰፋህ፤
እግሮቼም አልተሰነካከሉም።
38“ጠላቶቼን አሳደድሁ፤ አጠፋኋቸውም፤
እስኪጠፉም ድረስ ወደ ኋላ አልተመለስሁም።
39ፈጽሜ አጠፋኋቸው፤ ተመልሰውም መቆም አልቻሉም፤
ከእግሬም ሥር ወድቀዋል።
40ለጦርነት ኀይልን አስታጠቅኸኝ፣
ተቃዋሚዎቼንም ከእግሬ ሥር አንበረከክሃቸው።
41ጠላቶቼ ፊታቸውን አዙረው እንዲሸሹ አደረግሃቸው።
ባላንጣዎቼንም ደመሰስኋቸው።
42ለርዳታ ጮኹ፤ የሚያስጥላቸው ግን አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱ ግን
አልመለሰላቸውም።
43በምድር ላይ እንዳለ ትቢያ አደቀቅኋቸው፤
በመንገድም ላይ እንዳለ ጭቃ ወቀጥኋቸው፤ ረገጥኋቸውም።
44“በሕዝቤ ከተቃጣብኝ አደጋ አዳንኸኝ፤
የመንግሥታትም ራስ አደረግኸኝ።
የማላውቀውም ሕዝብ ተገዛልኝ፤
45የባዕድ አገር ሰዎች ይፈሩኛል፤
እንደ ሰሙኝም ወዲያውኑ ይታዘዙኛል።
46ባዕዳን ፈሩ፤
ከምሽጋቸውም እየተንቀጠቀጡ ወጡ#22፥46 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞችና የቩልጌቱ ቅጅ (እንዲሁም መዝ 18፥32 ይመ) ከዚህ ጋራ ይስማማሉ፤ ማሶሬቱ ግን ራሳቸውን ጐዱ ይላል።
47እግዚአብሔር ሕያው ነው! ዐለቴ የተባረከ ይሁን!
አምላኬ የድነቴ ዐለት ከፍ ከፍ ይበል።
48በቀሌን የሚመልስልኝ፣
አሕዛብንም ከሥሬ የሚያስገዛልኝ እርሱ ነው፤
49እርሱ ከጠላቶቼ እጅ ነጻ ያወጣኛል።
አንተ ከጠላቶቼ በላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤
ከጨካኝ ሰዎችም እጅ ታደግኸኝ።
50ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ፤
በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ስምህንም በመዝሙር እወድሳለሁ።
51“ለንጉሡ ታላቅ ድል ይሰጠዋል፤
ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ፣
ለዘላለም የማይለወጥ ፍቅሩን ያሳየዋል።”

Currently Selected:

2 ሳሙኤል 22: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in