1 ዜና መዋዕል 9
9
1እስራኤል ሁሉ በየትውልድ ሐረጋቸው ተቈጥረው ስማቸው በእስራኤል ነገሥታት መዝገብ ላይ ሰፈረ።
የኢየሩሳሌም ከተማ ሕዝብ
9፥1-17 ተጓ ምብ – ነህ 11፥3-19
የይሁዳ ሕዝብ ከፈጸሙት በደል የተነሣ ተማርከው ወደ ባቢሎን ተወሰዱ። 2በመጀመሪያ በየርስታቸውና በየከተሞቻቸው ተመልሰው የሰፈሩት ጥቂት እስራኤላውያን፣ ካህናት፣ ሌዋውያንና በቤተ መቅደሱ ውስጥ የጕልበት ሥራ የሚሠሩ አገልጋዮች ነበሩ።
3በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ የይሁዳ፣ የብንያም፣ የኤፍሬምና የምናሴ ነገዶች የሚከተሉት ናቸው፤
4ከይሁዳ ልጅ፣ ከፋሬስ ዘሮች፣ የባኒ ልጅ፣ የአምሪ ልጅ፣ የዖምሪ ልጅ፣ የዓሚሁድ ልጅ ዑታይ።
5ከሴሎናውያን#9፥5 ዘኍ 26፥20 ይመ፦
የበኵር ልጁ ዓሣያና ወንዶች ልጆቹ።
6ከዛራውያን፦
ይዑኤል፤
የሕዝቡ ቍጥር ስድስት መቶ ዘጠና ነበረ።
ከይሁዳ ነገድ የሰው ቍጥር ስድስት መቶ ዘጠና ነበር።
7ከብንያማውያን፦
የሐስኑአ ልጅ፣ የሆዳይዋ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ ሰሉ። 8የይሮሐም ልጅ ብኔያ፤ የሚክሪ ልጅ፣ የኦዚ ልጅ ኤላ፤ የይብንያ ልጅ፣ የራጉኤል ልጅ፣ የሰፋጥያ ልጅ ሜሱላም።
9በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ በተጻፈው መሠረት ከብንያም ነገድ የሕዝቡ ቍጥር ዘጠኝ መቶ ኀምሳ ስድስት ነበረ፤ እነዚህ ሁሉ ወንዶች የቤተ ሰብ አለቆች ነበሩ።
10ከካህናቱ፦
ዮዳኤ፣ ዮአሪብ፣ ያኪን፤
11የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የሆነው የአኪጦብ ልጅ፣ የመራዮት ልጅ፣ የሳዶቅ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ ዓዛርያስ።
12የመልክያ ልጅ፣ የፋስኮር ልጅ፣ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ፤ የኢሜር ልጅ፣ የምሺላሚት ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ፣ የየሕዜራ ልጅ፣ የዓዲኤል ልጅ መዕሣይ።
13የቤተ ሰብ አለቃ የነበሩት ካህናት ቍጥር አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ስድሳ ነበረ፤ እነዚህም በእግዚአብሔር ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት ብቁ ሰዎች ነበሩ።
14ከሌዋውያን ወገን፦
ከሜራሪ ዘሮች የአሳብያ ልጅ፣ የዓዝሪቃም ልጅ፣ የአሱብ ልጅ ሸማያ፣ 15በቅበቃር፣ ኤሬስ፣ ጋላልና የአሳፍ ልጅ፣ የዝክሪ ልጅ፣ የሚካ ልጅ መታንያ።
16የኤዶታም ልጅ፣ የጋላል ልጅ፣ የሰሙስ ልጅ አብድያ። እንዲሁም በነጦፋውያን ከተሞች የኖረው የሕልቃና ልጅ፣ የአሳ ልጅ በራክያ።
17የቤተ መቅደሱ በር ጠባቂዎች፦
ሰሎም፣ ዓቁብ፣ ጤልሞን፣ አሒማንና ወንድሞቻቸው፤ አለቃቸውም ሰሎም ነበረ፤ 18እርሱም በስተምሥራቅ በሚገኘው በንጉሡ በር እስካሁን ድረስ ተመድቧል። እነዚህም የሌዋውያኑ ሰፈር በር ጠባቂዎች ነበሩ።
19የቆሬ ልጅ የአብያሳፍ ልጅ፣ የቆሬ ልጅ ሰሎምና ከርሱም ቤተ ሰብ የሆኑት ቆሬያውያን ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ#9፥19 በዚህ በቍጥር 21 እና 23 ላይ ቤተ መቅደሱን ያመለክታል። የሚያስገባውን በር ይጠብቁ እንደ ነበር ሁሉ፣ እነዚህም ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ ነበር።
20በቀድሞ ጊዜ የበር ጠባቂዎቹ አለቃ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ነበረ፤ እግዚአብሔርም ከርሱ ጋራ ነበረ።
21ወደ መገናኛው ድንኳን የሚያስገባውን በር የሚጠብቀው ደግሞ የሜሱላም ልጅ ዘካርያስ ነበረ።
22መግቢያ በሮቹን በኀላፊነት እንዲጠብቁ የተመረጡት በአጠቃላይ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ።
እነርሱም በትውልድ ሐረጋቸው መሠረት በሚኖሩባቸው መንደሮች ተቈጥረው ተመዘገቡ፤ በር ጠባቂዎቹን በዚያ ቦታ ላይ የመደቧቸው ዳዊትና ባለራእዩ ሳሙኤል ነበሩ። 23የማደሪያውን ድንኳን፣ ማለትም የእግዚአብሔርን ቤት የሚጠብቁትም እነርሱና ዘሮቻቸው ነበሩ። 24በር ጠባቂዎቹም በምሥራቅ፣ በምዕራብ፣ በሰሜንና፣ በደቡብ በሚገኙት በአራቱም ማእዘኖች ላይ ነበሩ። 25ወንድሞቻቸውም በየመንደሮቻቸው ሆነው በየጊዜው እየወጡ የጥበቃውን ሥራ ሰባት ሰባት ቀን ያግዟቸው ነበር። 26ሌዋውያን የነበሩት አራቱ የበር ጠባቂ አለቆች ግን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሚገኙትን ክፍሎችና ግምጃ ቤቶች በኀላፊነት ይጠብቁ ነበር። 27የጥበቃውን ሥራ የሚያከናውኑት እነርሱ በመሆናቸው የሚያድሩትም በዚያው በእግዚአብሔር ቤት አካባቢ ነበረ፤ ጧት ጧትም ደጆቹን የሚከፍቱት እነርሱ ነበሩ።
28ከእነርሱም አንዳንዶቹ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በኀላፊነት ይጠብቁ ነበር፤ ዕቃዎቹም በሚገቡበትና በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ ይቈጥሩ ነበር። 29ሌሎቹ ሌዋውያን ደግሞ ዕቃዎቹንና የቤተ መቅደሱን ንዋያተ ቅድሳት፣ ዱቄቱን፣ የወይን ጠጁን፣ የወይራ ዘይቱን፣ ዕጣኑን፣ የሽቱውን ቅመማ ቅመም እንዲጠብቁ ተመድበው ነበር። 30ከካህናቱም አንዳንዶቹ የሽቱውን ቅመማ ቅመም ይለውሱና ያዘጋጁ ነበር። 31የቆሬያዊው የሰሎም በኵር ልጅ ሌዋዊው ማቲትያ የቍርባኑን እንጀራ የመጋገር ኀላፊነት ተሰጥቶት ነበር። 32በየሰንበቱ ለሚዘጋጀው ገጸ ኅብስትም ኀላፊነቱ የተሰጠው ከቀዓታውያን ወንድሞቻቸው መካከል ለአንዳንዶቹ ነበር።
33የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች የነበሩት መዘምራኑ ደግሞ በቤተ መቅደሱ ክፍሎች ውስጥ እንዲኖሩና ከሌላው ሥራ ሁሉ ነጻ እንዲሆኑ ተደርጎ ነበር፤ ምክንያቱም ቀንና ሌሊት የሚሠሩት ሥራ ነበራቸው።
34እነዚህ ሁሉ የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ሲሆኑ፣ በትውልድ ሐረጋቸው መሠረት ተመዘገቡ፤ የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።
የሳኦል ትውልድ ሐረግ
9፥34-44 ተጓ ምብ – 1ዜና 8፥28-38
35የገባዖን አባት#9፥35 አባት ማለት፣ የማኅበረ ሰብ መሪ ወይም፣ የጦር መሪ ማለት ነው። ይዒኤል በገባዖን ኖረ፤
የሚስቱም ስም መዓካ ይባላል። 36የበኵር ልጁም አብዶን ይባል ነበር፤ የእርሱም ተከታዮች ጹር፣ ቂስ፣ ባኣል፣ ኔር፣ ናዳብ፣ 37ጌዶር፣ አሒዮ፣ ዘካርያስ እና ሚቅሎት ነበሩ። 38ሚቅሎት ሺሜዓን ወለደ፤ እነርሱም ደግሞ ከሥጋ ዘመዶቻቸው ጋራ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።
39ኔርም ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፣ ሜልኪሳን፣ አሚናዳብን፣ አስበኣልን#9፥39 ኢሽቦሼት በመባልም ይታወቃል። ወለደ።
40የዮናታን ወንድ ልጅ
መሪበኣል#9፥40 ሜፊቦስቴ በመባልም ይታወቃል። ነው፤ መሪበኣልም ሚካን ወለደ።
41የሚካ ወንዶች ልጆች፤
ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታሬዓ፣ አካዝ።
42አካዝ የዕራን ወለደ፤ የዕራም ዓሌሜትን፣ ዓዝሞትን፣ ዚምሪን ወለደ፤ ዚምሪን ሞጻን ወለደ። 43ሞጻ ቢንዓን ወለደ፤ ልጁ ረፋያ ነበረ፤ ልጁ ኤልዓሣ፣ ልጁ ኤሴል።
44ኤሴል ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም፦
ዓዝሪቃም፣ ቦክሩ፣ እስማኤል፣ ሸዓርያ፣ አብድዩ፣ ሐናን ይባላል፤ እነዚህ የኤሴል ወንዶች ልጆች ናቸው።
Currently Selected:
1 ዜና መዋዕል 9: NASV
Highlight
Share
Copy

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.