1
የዮሐንስ ራእይ 13:18
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
ጥበብ በዚህ አለ። አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፤ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው።
Compare
Explore የዮሐንስ ራእይ 13:18
2
የዮሐንስ ራእይ 13:8
ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል።
Explore የዮሐንስ ራእይ 13:8
3
የዮሐንስ ራእይ 13:16-17
ታናናሾችና ታላላቆችም ባለጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥ የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል።
Explore የዮሐንስ ራእይ 13:16-17
4
የዮሐንስ ራእይ 13:10
ይማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል። የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት በዚህ ነው።
Explore የዮሐንስ ራእይ 13:10
5
የዮሐንስ ራእይ 13:1
አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ ዐሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፤ በቀንዶቹም ላይ ዐሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።
Explore የዮሐንስ ራእይ 13:1
6
የዮሐንስ ራእይ 13:7
ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፤ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።
Explore የዮሐንስ ራእይ 13:7
7
የዮሐንስ ራእይ 13:14-15
በአውሬውም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቍስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲያደርጉ በምድር የሚኖሩትን ይናገራል። የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።
Explore የዮሐንስ ራእይ 13:14-15
8
የዮሐንስ ራእይ 13:2
ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኀይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።
Explore የዮሐንስ ራእይ 13:2
9
የዮሐንስ ራእይ 13:5
ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፤ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።
Explore የዮሐንስ ራእይ 13:5
10
የዮሐንስ ራእይ 13:3
ከራሶቹም ለሞት እንደ ታረደ ሆኖ አንዱን አየሁ፤ ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰ። ምድርም ሁሉ አውሬውን እየተከተለ ተደነቀ፤
Explore የዮሐንስ ራእይ 13:3
11
የዮሐንስ ራእይ 13:11-12
ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፤ የበግ ቀንዶችን የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት እንደ ዘንዶም ይናገር ነበር። በፊተኛውም አውሬ ሥልጣን በእርሱ ፊት ሁሉን ያደርጋል። ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰለት፤ ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል።
Explore የዮሐንስ ራእይ 13:11-12
Home
Bible
Plans
Videos