1
የዮሐንስ ራእይ 12:11
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
እነርሱም በበጉ ደም በምስክራቸውም ቃል ድል ነሡት፤ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም።
Compare
Explore የዮሐንስ ራእይ 12:11
2
የዮሐንስ ራእይ 12:10
ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ፤ እንዲህ ሲል “አሁን የአምላካችን ማዳንና ኀይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፤ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸውየወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።
Explore የዮሐንስ ራእይ 12:10
3
የዮሐንስ ራእይ 12:9
ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።
Explore የዮሐንስ ራእይ 12:9
4
የዮሐንስ ራእይ 12:12
ስለዚህ ሰማይና በውስጡ የምታድሩ ሆይ! ደስይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፤ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።”
Explore የዮሐንስ ራእይ 12:12
5
የዮሐንስ ራእይ 12:7
በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፤
Explore የዮሐንስ ራእይ 12:7
6
የዮሐንስ ራእይ 12:17
ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤
Explore የዮሐንስ ራእይ 12:17
7
የዮሐንስ ራእይ 12:1-2
ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ፤ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የዐሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የተቀዳጀች አንዲት ሴት ነበረች። እርስዋም ፀንሳ ነበር፤ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጭንቃ ጮኸች።
Explore የዮሐንስ ራእይ 12:1-2
8
የዮሐንስ ራእይ 12:5-6
አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ። ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሓ ሸሸች።
Explore የዮሐንስ ራእይ 12:5-6
9
የዮሐንስ ራእይ 12:3-4
ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ ይኸውም ታላቅ ቀይ ዘንዶነው፤ ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶችም ነበሩት፤ በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ፤ ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።
Explore የዮሐንስ ራእይ 12:3-4
10
የዮሐንስ ራእይ 12:14-16
ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሓ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት። እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ የሚያህልን ውሃ ከአፉ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ። ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት፤ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው።
Explore የዮሐንስ ራእይ 12:14-16
Home
Bible
Plans
Videos