1
ኦሪት ዘዳግም 11:19
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ልጆቻችሁንም አስተምሯቸው፤ ቤት ስትቀመጥ፥ መንገድ ስትሄድ፥ ስትተኛና ስትነሣ ስለዚህ አጫውታቸው።
Compare
Explore ኦሪት ዘዳግም 11:19
2
ኦሪት ዘዳግም 11:18
“እነዚህን ቃሎቼን፥ በልባችሁና በአእምሮአችሁ አኑሯቸው፤ በእጆቻችሁ ላይ ምልክት አድርጋችሁ እሰሯቸው፥ በግምባራችሁም ላይ ይሁኑ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 11:18
3
ኦሪት ዘዳግም 11:13-14
“ጌታ አምላክህን በመውደድ ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዞች በታማኝነት ብትጠብቁ፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁም እርሱን በማገልገል፥ በታማኝነት ብትጠብቁ፥ እህልህን፥ ወይንህንና ዘይትህን እንድትሰበስብ የበልጉንና የክረምቱን ዝናብ በምድርህ ላይ በየወቅቱ አዘንባለሁ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 11:13-14
4
ኦሪት ዘዳግም 11:1
“እንግዲህ ጌታ አምላክህን ውደድ፤ ግዴታውን፥ ሥርዓቱን፥ ሕጉንና ትእዛዙን ሁልጊዜ ጠብቅ።
Explore ኦሪት ዘዳግም 11:1
5
ኦሪት ዘዳግም 11:26-28
“እነሆ፤ ዛሬ በረከትንና መርገምን በፊታችሁ አኖራለሁ፤ በረከቱ ዛሬ የምሰጣችሁን የጌታ የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ስትፈጽሙ ሲሆን፥ መርገሙ ደግሞ፥ የጌታ የአምላካችሁን ትእዛዞች የማትፈጽሙ፥ የማታውቋቸውንም ሌሎች አማልክት ለመከተል እኔ ከማዛችሁ መንገድ የምትወጡ ከሆነ ነው።”
Explore ኦሪት ዘዳግም 11:26-28
6
ኦሪት ዘዳግም 11:20-21
በቤትህ መቃኖችና በግቢህ በሮች ላይ ጻፋቸው፤ ይህን ካደረጋችሁ፥ ጌታ ለአባቶቻችሁ ለመስጠት በማለላቸው ምድር የእናንተና የልጆቻችሁ ዘመን ከምድር በላይ ያሉ ሰማያትን ርቀት ያህል ይሆናል።”
Explore ኦሪት ዘዳግም 11:20-21
7
ኦሪት ዘዳግም 11:16
ተጠንቀቁ! ተታላችሁ ሌሎች አማልክትን እንዳታመልኩ፤ እንዳትሰግዱላቸውም።
Explore ኦሪት ዘዳግም 11:16
Home
Bible
Plans
Videos