1
መጽሐፈ ምሳሌ 3:5-6
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
በሙሉ ልብህ በእግዚአብሔር ታመን እንጂ በራስህ ዕውቀት አትመካ። በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔርን መሪ አድርገው፤ እርሱም በትክክለኛው መንገድ ይመራሃል።
Compare
Explore መጽሐፈ ምሳሌ 3:5-6
2
መጽሐፈ ምሳሌ 3:7
“እኔ ዐዋቂ ነኝ” አትበል። ይልቅስ እግዚአብሔርን ፍራ፤ ከክፋትም ራቅ።
Explore መጽሐፈ ምሳሌ 3:7
3
መጽሐፈ ምሳሌ 3:9-10
ከሀብትህና ምድርህ ከሚያፈራው መልካም ነገር ሁሉ የመጀመሪያውን መባ አድርገህ በመስጠት እግዚአብሔርን አክብር። ይህን ብታደርግ ጐተራዎችህ በእህል የተሞሉ ይሆናሉ፤ የወይን መጥመቂያህም በአዲስ የወይን ጠጅ ሞልቶ ይትረፈረፋል።
Explore መጽሐፈ ምሳሌ 3:9-10
4
መጽሐፈ ምሳሌ 3:3
ታማኝነትና እውነተኛነትን አትተው፤ እንደ አንገት ሐብል ተጠንቅቀህ ያዛቸው፤ በልብህም ሰሌዳ ጻፋቸው።
Explore መጽሐፈ ምሳሌ 3:3
5
መጽሐፈ ምሳሌ 3:11-12
ልጄ ሆይ! የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ፤ በሚገሥጽህም ጊዜ አትመረር። አባት የሚወደውን ልጁን እንደሚገሥጽ እግዚአብሔርም የሚወዳቸውን ሰዎች ይገሥጻል።
Explore መጽሐፈ ምሳሌ 3:11-12
6
መጽሐፈ ምሳሌ 3:1-2
ልጄ ሆይ! የማስተምርህን አትርሳ፤ ትእዛዞቼንም በልብህ ጠብቅ። የእኔ ትምህርት ረጅም ዕድሜን ከብዙ ተድላና ደስታ ጋር ይሰጥሃል።
Explore መጽሐፈ ምሳሌ 3:1-2
7
መጽሐፈ ምሳሌ 3:13-15
ጥበብን የሚያገኝ፥ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ ሰው የተባረከ ነው። ስለዚህ ጥበብ ከብር ይበልጥ ትርፍ ትሰጣለች፤ ከወርቅም የተሻለ ጥቅም ታስገኛለች። ጥበብ ከውድ ዕንቊ ትከብራለች፤ አንተ ለማግኘት ከምትመኛቸው ነገሮች ሁሉ እርስዋን የሚወዳደራት ከቶ የለም።
Explore መጽሐፈ ምሳሌ 3:13-15
8
መጽሐፈ ምሳሌ 3:27
ርዳታ እንድታደርግለት ለሚገባው ሰው ዐቅምህ በሚፈቅድልህ መጠን በጎ ነገር ከማድረግ አትቈጠብ።
Explore መጽሐፈ ምሳሌ 3:27
9
መጽሐፈ ምሳሌ 3:19
እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ፤ በማስተዋልም ሰማያትን አጸና።
Explore መጽሐፈ ምሳሌ 3:19
Home
Bible
Plans
Videos