1
መጽሐፈ ኢያሱ 10:13
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፤ ጨረቃም ካለችበት ሳትንቀሳቀስ ቈየች፤ ይህም በያሻር መጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል። ሳይንቀሳቀስ በሰማይ መካከል ቆመ፤ ቀኑንም ሙሉ ሳይጠልቅ ቈየ፤
Compare
Explore መጽሐፈ ኢያሱ 10:13
2
መጽሐፈ ኢያሱ 10:12
እግዚአብሔር አሞራውያንን ለእስራኤላውያን አሳልፎ በሰጠበት ቀን ኢያሱ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገረ፤ እርሱም በእስራኤል ፊት እንዲህ አለ፦ “ፀሐይ በገባዖን፥ ጨረቃም በኤሎን ሸለቆ ላይ ይቁሙ” አለ።
Explore መጽሐፈ ኢያሱ 10:12
3
መጽሐፈ ኢያሱ 10:14
እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት፥ እንደዚያ ያለ ቀን፥ ከዚያም በፊት ሆነ ከዚያ ወዲህ ታይቶ አይታወቅም፤ በእርግጥም እግዚአብሔር ከእስራኤል ጐን ተሰልፎ ይዋጋላቸው ነበር።
Explore መጽሐፈ ኢያሱ 10:14
4
መጽሐፈ ኢያሱ 10:8
እግዚአብሔርም ኢያሱን “እነርሱን አትፍራቸው፤ እኔ አንተን በእነርሱ ላይ ድልን አቀዳጅሃለሁ፤ ከእነርሱ አንድም የሚቋቋምህ አይኖርም” አለው።
Explore መጽሐፈ ኢያሱ 10:8
5
መጽሐፈ ኢያሱ 10:25
ኢያሱም ለጦር መኰንኖቹ እንዲህ አለ፤ እግዚአብሔር ጦርነት በምትገጥሙአቸው በጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ ልክ እንደዚህ ስለሚያደርግ አትፍሩ አይዞአችሁ፤ ቆራጥነትና ድፍረት ይኑራችሁ።
Explore መጽሐፈ ኢያሱ 10:25
Home
Bible
Plans
Videos