1
መጽሐፈ መክብብ 12:13
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
እነሆ፥ ሁሉ ነገር ተነግሮአል፤ የሁሉ ነገር መደምደሚያ ይህ ነው፤ እግዚአብሔርን ፍራ፤ ትእዛዞቹንም ጠብቅ፤ ይህ የሰው ዋና ተግባሩ ነው።
Compare
Explore መጽሐፈ መክብብ 12:13
2
መጽሐፈ መክብብ 12:14
እግዚአብሔር ስውር የሆነውን ነገር ሳይቀር የሰውን ሥራ ሁሉ ክፉውንም ደጉንም ወደ ፍርድ ያመጣዋል።
Explore መጽሐፈ መክብብ 12:14
3
መጽሐፈ መክብብ 12:1-2
በወጣትነትህ ዘመን ፈጣሪህን አስብ፤ ይህን ባታደርግ ግን ክፉ ቀን ይመጣብሃል፤ “ደስ አያሰኙኝም” የምትላቸው ዓመቶች ይደርሳሉ። የፀሐይ፥ የጨረቃና የከዋክብት ብርሃን ለአንተ የሚጨልምበት ጊዜ ይመጣል፤ ያን ጊዜ ከዝናብ በኋላ ደመናዎች ከስፍራቸው ፈቀቅ አይሉም፤
Explore መጽሐፈ መክብብ 12:1-2
4
መጽሐፈ መክብብ 12:6-7
የብር ሐብል ይበጠሳል፤ ከወርቅ የተሠራ መቅረዝ ወድቆ ይሰበራል፤ የውሃ መቅጃውን የያዘ ገመድ በውሃ ጒድጓድ ላይ ይበጠሳል፤ የውሃ መቅጃውም እንስራ ይከሰከሳል፤ ሥጋ ዐፈር ስለ ሆነ ወደ ዐፈር ይመለሳል፤ ነፍስም ወደ ፈጠራት ወደ እግዚአብሔር ትሄዳለች።
Explore መጽሐፈ መክብብ 12:6-7
5
መጽሐፈ መክብብ 12:8
ጥበበኛው፥ “ከንቱ! ከንቱ! ሁሉ ነገር ከንቱ ነው!” አለ።
Explore መጽሐፈ መክብብ 12:8
Home
Bible
Plans
Videos