1
ትንቢተ ዳንኤል 9:4
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር በመናዘዝ እንዲህ ስል ጸለይኩ፦ “ለሚወዱህና ትእዛዞችህን ለሚጠብቁ ቃል ኪዳንህንና ዘለዓለማዊ ፍቅርህን የምትጠብቅ ታላቅና መፈራት የሚገባህ አንተ ጌታ እግዚአብሔር ነህ።
Compare
Explore ትንቢተ ዳንኤል 9:4
2
ትንቢተ ዳንኤል 9:18-19
አምላክ ሆይ! እባክህ አድምጠኝ፤ የእኛን ችግርና በስምህ የምትጠራውን ከተማ ጥፋት ተመልከት፤ ወደ አንተ የምንጸልየው የአንተን ምሕረት በመተማመን እንጂ በእኛ መልካም ሥራ በመመካት አይደለም። እግዚአብሔር ሆይ! ስማን! እግዚአብሔር ሆይ! ይቅር በለን! እባክህ አድምጠን! ሥራህንም ግለጥ! አምላክ ሆይ! አትዘግይ፤ ይህች ከተማና ይህ ሕዝብ በስምህ የተጠሩ ናቸው።”
Explore ትንቢተ ዳንኤል 9:18-19
3
ትንቢተ ዳንኤል 9:3
ማቅ ለብሼና ዐመድ ላይ ተቀምጬ በመጾም ጸሎቴንና ልመናዬን ለማቅረብ ፊቴን ወደ ጌታ እግዚአብሔር መለስኩ።
Explore ትንቢተ ዳንኤል 9:3
4
ትንቢተ ዳንኤል 9:9
ጌታ አምላካችን ሆይ፥ ምንም እኛ በአንተ ላይ ብናምፅ አንተ መሐሪና ይቅር ባይ ነህ።
Explore ትንቢተ ዳንኤል 9:9
5
ትንቢተ ዳንኤል 9:27
ያም መሪ ለአንድ ሳምንት ከብዙ ሕዝቦች ጋር የጠበቀ ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ በሳምንቱም እኩሌታ መሥዋዕቱንና ቊርባኑን ያስቀራል፤ በእነርሱም ፈንታ ጥፋት የሚያስከትለው ርኲሰት እንዲተካ ያደርጋል። ይህም የሚሆነው በዚያ አጥፊ መሪ ላይ የታወጀው ቅጣት እስኪፈጸም ድረስ ነው።”
Explore ትንቢተ ዳንኤል 9:27
Home
Bible
Plans
Videos