1
ኢሳይያስ 11:2-3
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
NASV
የእግዚአብሔር መንፈስ፣ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፣ የምክርና የኀይል መንፈስ፣ የዕውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል። እግዚአብሔርን በመፍራት ደስ ይለዋል።
Compare
Explore ኢሳይያስ 11:2-3
2
ኢሳይያስ 11:1
ከእሴይ ግንድ ቍጥቋጥ ይወጣል፤ ከሥሮቹም አንዱ ቅርንጫፍ ፍሬ ያፈራል።
Explore ኢሳይያስ 11:1
3
ኢሳይያስ 11:4
ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤ በአፉ በትር ምድርን ይመታል፤ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
Explore ኢሳይያስ 11:4
4
ኢሳይያስ 11:5
ጽድቅ የወገቡ መታጠቂያ፣ ታማኝነትም የጐኑ መቀነት ይሆናል።
Explore ኢሳይያስ 11:5
5
ኢሳይያስ 11:9
በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ ጕዳት ወይም ጥፋት አያደርሱም፤ ውሃ ባሕርን እንደሚሸፍን፣ ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።
Explore ኢሳይያስ 11:9
6
ኢሳይያስ 11:6
ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋራ ይኖራል፤ ነብርም ከፍየል ግልገል ጋራ ይተኛል፤ ጥጃ፣ የአንበሳ ደቦልና የሠባ ከብት በአንድነት ይሰማራሉ፤ ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል።
Explore ኢሳይያስ 11:6
7
ኢሳይያስ 11:10
በዚያም ቀን፣ የእሴይ ሥር ለሕዝቦች ምልክት ሆኖ ይቆማል፤ አሕዛብ እርሱን ይፈልጋሉ፤ ማረፊያውም የከበረ ይሆናል።
Explore ኢሳይያስ 11:10