1
መክብብ 12:13
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
NASV
እነሆ፤ ሁሉ ነገር ከተሰማ ዘንድ፣ የነገሩ ሁሉ ድምዳሜ ይህ ነው፤ አምላክን ፍራ፤ ትእዛዞቹንም ጠብቅ፤ ይህ የሰው ሁለንተናዊ ተግባሩ ነውና።
Compare
Explore መክብብ 12:13
2
መክብብ 12:14
መልካምም ይሁን ክፉ፣ ስውር የሆነውን ነገር ሁሉ አንድ ሳይቀር፣ ማንኛውንም ሥራ አምላክ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና።
Explore መክብብ 12:14
3
መክብብ 12:1-2
የጭንቀት ጊዜ ሳይመጣ፣ “ደስ አያሰኙኝም” የምትላቸው ዓመታት ሳይደርሱ፣ በወጣትነትህ ጊዜ፣ ፈጣሪህን ዐስብ። ፀሓይና ብርሃን፣ ጨረቃና ከዋክብት ሳይጨልሙ፣ ደመናትም ከዝናብ በኋላ ሳይመለሱ፣
Explore መክብብ 12:1-2
4
መክብብ 12:6-7
የብር ሰንሰለት ሳይበጠስ፣ የወርቅ ሳሕንም ሳይሰበር፣ የውሃ መቅጃው በምንጩ አጠገብ ሳይከሰከስ፣ ወይም መንኰራኵሩ በውሃ ጕድጓድ ላይ ሳይሰበር፣ ዐፈር ወደ መጣበት መሬት ሳይመለስ፣ መንፈስም ወደ ሰጠው ወደ አምላክ ሳይመለስ፣ ፈጣሪህን ዐስብ።
Explore መክብብ 12:6-7
5
መክብብ 12:8
ሰባኪው “ከንቱ ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ ነው!” ይላል።
Explore መክብብ 12:8