1
ኦሪት ዘፍጥረት 32:28
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ሰውየውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ከእግዚአብሔርም ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃል፤ ስለዚህ ስምህ ‘እስራኤል’ ይባላል” አለው።
Vergelyk
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 32:28
2
ኦሪት ዘፍጥረት 32:26
ከዚህ በኋላ ሰውየው “ሌሊቱ ሊነጋ ስለ ሆነ ልቀቀኝ” አለ። ያዕቆብም “ካልባረክኸኝ አለቅህም” አለው።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 32:26
3
ኦሪት ዘፍጥረት 32:24
እርሱ ግን በስተማዶ ለብቻው ቀረ፤ ከዚህ በኋላ ሌሊቱ እስኪነጋ ድረስ አንድ ሰው ሲታገለው ዐደረ።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 32:24
4
ኦሪት ዘፍጥረት 32:30
ያዕቆብም “እኔ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አይቼ እነሆ፥ በሕይወት እገኛለሁ” አለ። በዚህም ምክንያት ያንን ቦታ “ጵንኤል” ብሎ ጠራው።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 32:30
5
ኦሪት ዘፍጥረት 32:25
ያ ሰው ያዕቆብን በትግል ማሸነፍ እንዳቃተው ባየ ጊዜ የጭኑን ሹልዳ መታው፤ ያዕቆብም በሚታገልበት ጊዜ ጭኑ ከመገጣጠሚያው ላይ ተለያየ፤
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 32:25
6
ኦሪት ዘፍጥረት 32:27
ሰውየውም “ስምህ ማን ነው?” አለው። “ስሜ ያዕቆብ ነው” አለው።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 32:27
7
ኦሪት ዘፍጥረት 32:29
ያዕቆብም “አንተስ ስምህ ማን ነው?” አለው። ሰውየውም “ስሜን ለማወቅ የምትፈልገው ለምንድን ነው?” አለውና ያዕቆብን ባረከው።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 32:29
8
ኦሪት ዘፍጥረት 32:10
እኔ ባሪያህ ይህን ያኽል ቸርነትና ታማኝነት ልታሳየኝ የሚገባኝ አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ተሻግሬ ስመጣ ከምመረኰዘው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን እነዚህን በሁለት ቡድን የተከፈሉ ወገኖች ይዤ ተመልሻለሁ።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 32:10
9
ኦሪት ዘፍጥረት 32:32
ያዕቆብ ከሰውየው ጋር ሲታገል ሰውየው ሹልዳውን መቶት ስለ ነበር እስራኤላውያን እስከ ዛሬ ድረስ በጭን መጋጠሚያ ላይ ያለውን የሹልዳ ሥጋ አይበሉም።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 32:32
10
ኦሪት ዘፍጥረት 32:9
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ ጸለየ፤ “የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ ሆይ! ልመናዬን አድምጥ፤ አምላክ ሆይ፥ ‘ወደ ትውልድ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ፤ እዚያም መልካም ነገር እንዲሆንልህ አደርጋለሁ’ ብለኸኝ ነበር።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 32:9
11
ኦሪት ዘፍጥረት 32:11
በእኔ ላይ አደጋ በመጣል ሴቶችና ሕፃናት እንኳ ሳይቀሩ ያጠፋናል ብዬ ስለ ፈራሁ ከወንድሜ ከዔሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 32:11
Tuisblad
Bybel
Leesplanne
Video's