1
ኦሪት ዘፍጥረት 21:1
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ስለዚህ እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት ለሣራ መልካም በማድረግ የገባውን ቃል ኪዳን ፈጸመላት።
Vergelyk
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 21:1
2
ኦሪት ዘፍጥረት 21:17-18
እግዚአብሔርም ልጁ ምርር ብሎ ሲያለቅስ ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን “አጋር ሆይ፤ የምትጨነቂበት ነገር ምንድን ነው? እግዚአብሔር የልጁን ለቅሶ ሰምቶአልና አይዞሽ አትፍሪ፤ ተነሺ፤ ሂጂና ልጁን አንሥተሽ ዕቀፊው የእርሱንም ዘር አበዛለሁ፤ ታላቅም ሕዝብ አደርገዋለሁ” አላት።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 21:17-18
3
ኦሪት ዘፍጥረት 21:2
ስለዚህም ፀንሳ በእርጅናው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ልጁም የተወለደው “በዚህ ጊዜ ይወለዳል” ብሎ እግዚአብሔር በተናገረበት ጊዜ ነው።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 21:2
4
ኦሪት ዘፍጥረት 21:6
ሣራ “እግዚአብሔር ደስታና ሳቅ አመጣልኝ፤ ስለዚህ ይህን ነገር የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋር ይስቃል” አለች።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 21:6
5
ኦሪት ዘፍጥረት 21:12
እግዚአብሔር ግን አብርሃምን “ስለ ልጁና ስለ አገልጋይቱ ስለ አጋር አትጨነቅ፤ ዘር የሚወጣልህ በይስሐቅ በኩል ስለ ሆነ ሣራ የምትልህን ሁሉ አድርግ፤
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 21:12
6
ኦሪት ዘፍጥረት 21:13
የአገልጋይቱም ልጅ የአንተ ልጅ ስለ ሆነ ታላቅ ሕዝብ እስኪሆን ድረስ ዘሩን አበዛለሁ” አለው።
Verken ኦሪት ዘፍጥረት 21:13
Tuisblad
Bybel
Leesplanne
Video's