1
የሉቃስ ወንጌል 8:15
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
በመልካም መሬት ላይ ያሉት ደግሞ ቃሉን በመልካምና በቅን ልብ ሰምተው የሚጠብቁ፥ በመጽናትም ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።
Paghambingin
I-explore የሉቃስ ወንጌል 8:15
2
የሉቃስ ወንጌል 8:14
በእሾህም መካከል የወደቁት እንዲሁ ከእነዚያ ከሰሙት ወገን ናቸው፤ በመንገዳቸውም በዚህ የምድራዊ ሕይወት ምኞትና ሀብት እንዲሁም ምቾት ይታነቃሉ፤ ሙሉ ፍሬም አያፈሩም።
I-explore የሉቃስ ወንጌል 8:14
3
የሉቃስ ወንጌል 8:13
እንዲሁም በዐለት ላይ ያሉት ቃሉን በሰሙ ጊዜ በደስታ የሚቀበሉት ናቸው፤ ነገር ግን ሥር የላቸውም፥ እነርሱም ለጊዜው ብቻ ያምናሉ እንጂ በፈተና ጊዜ ይክዳሉ።
I-explore የሉቃስ ወንጌል 8:13
4
የሉቃስ ወንጌል 8:25
እርሱም፦ “እምነታችሁ የት አለ?” አላቸው። በፍርሃትና በመደነቅ ተውጠውም፤ እርስ በርሳቸው፦ “እንዲህ ነፋሳትንና ውኃን ሳይቀር የሚያዝ፥ እነርሱም የሚታዘዙለት ይህ ለመሆኑ ማን ነው?” ተባባሉ።
I-explore የሉቃስ ወንጌል 8:25
5
የሉቃስ ወንጌል 8:12
በመንገድ ዳርም ያሉት የሰሙት ናቸው፤ ከዚያ በኋላም አምነው እንዳይድኑ ዲያብሎስ መጥቶ ቃሉን ከልባቸው ይወስዳል።
I-explore የሉቃስ ወንጌል 8:12
6
የሉቃስ ወንጌል 8:17
የማይገለጥ ምንም የተሰወረ የማይታወቅም ወደ ብርሃንም የማይመጣ ምንም የተሸሸገ ነገር የለምና።
I-explore የሉቃስ ወንጌል 8:17
7
የሉቃስ ወንጌል 8:47-48
ሴቲቱም መደበቅ እንዳልቻለች ባወቀች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች መጥታ በፊቱ ተደፋች፤ በምን ምክንያት እንደ ዳሰሰችውና እንዴት ፈጥና እንደ ተፈወሰች በሕዝቡ ሁሉ ፊት አወራች። እርሱም፦ “ልጄ ሆይ! እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤” አላት።
I-explore የሉቃስ ወንጌል 8:47-48
8
የሉቃስ ወንጌል 8:24
ቀርበውም፦ “መምህር ሆይ! መምህር ሆይ! እየጠፋን ነው፤” እያሉ ቀሰቀሱት። እርሱም ነቅቶ ነፋሱንና የሚናውጠውን የውኃ ሞገድ ገሠጻቸው፤ እነርሱም አቆሙ፤ ጸጥታም ሆነ።
I-explore የሉቃስ ወንጌል 8:24
Home
Biblia
Mga Gabay
Mga Palabas