ክርስቶስ የመጨረሻችን ንግስት አስቴርSample

የክርስቶስ በእኛ ሁኔታ መሆን
የአስቴር ታሪክ እኛ ሁላችን ወደዚህ ዓለም ስንወለድ መለወጥ ወይም መቀልበስ የማንችለው አቅመ ቢስ እንደሆንን፤ በመንፈሳዊ ሞት ውርስ አካለ ስንኩላን መሆናችንን ያሳስበናል፡፡ የእርሷ ታሪክ በነገር ሁሉ እንደ እኛ ሰው የሆነውን፤ በመንፈሳዊ አለመቻላችን ደግሞ በእኛ ሁኔታ ራሱን የገለፀውን ክርስቶስን እንድናስብ ያደርገናል፡፡
በመላው ፋርስ ያሉ አይሁዶች ማቅ ለብሰው፤ አመድ ነስንሰው እያለቀሱና እየጾሙ በሐማ የዘር ማጥፋት ሴራ ተስፋ መቁረጣቸውን የሚያሳይን ታሪክ እንመለከታለን፡፡ መርደኪዮስም እዚያው በንጉሱ በር መግቢያ ሊታይ እንደሚችል እያወቀ ልክ እንደዛው አደረገ፡፡ ነገሩ ለአስቴር እንደደረሳት መርደኪዮስ ምን እያደረገ እንዳለ ለማረጋገጥ ረዳቷን አክራቲዮስን ላከችው፡፡ በዚህ ጊዜ ሀማ ህዝቧን ሊያጠፋ ክፉ ዕቅድ እንዳቀደ አወቀች፡፡ መርደኪዮስም ስለ ህዝቡ በአስቸኳይ ወደ ንጉሱ ገብታ ትለምን ዘንድ መልዕክት ላከባት፡፡ አስቴርም በመርደኪዮስ ተቆጣች፤ ምክንያቱም ንጉሱ ሳይጋብዘው ማንም ወደ እርሱ ቢገባ የሞት ቅጣት ይፈረድበታልና፡፡ መርደኪዮስ ግን ያለማቋረጥ ግድ አላት፡፡ አስቴር በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ያላትን ልዩና ትልቅ ስፍራ በማስታወስ “ምናልባት የተወለድሽው ለዚህ ጊዜ ነው” በማለት ያነሳሳታል።
ይህ የጥፋት አዋጅ ከመሆኑ በፊት ነበር እግዚአብሔር አስቴርን ወደ መንግስትነት ያመጣት፤ ስለሆነም በዚህ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እንድትረዳቸው ነው የሾማት፡፡ በዚህ ወቅት አስቴር ለአራት ዓመታት ያህል ንግስት ነበረች፤ ይሁን እንጂ በዚህ ሁሉ ጊዜ ግን ከንጉሳውያን ዘንድ አስቴር አይሁድ ስለመሆኗ የሚያውቅ አልነበረም፡፡ ራሷን ከህዝቧ ጋር በመለየት እጅግ ከባድ የስጋት ውሳኔ ወሰነች፤ ይኸውም ብቸኛ እነርሱን ልትረዳ የምትችልበት መንገድ መሆኑን ግን ተረድታለች፡፡ አስቴም ለመርደኪዮስ መልሳ ሁሉም በሱዛ የሚገኙ አይሁዳውያን በሙሉ ስለ እኔ ይፁሙ የሚል መልዕክት ላከች፡፡
ኢየሱስን እንደገና በዚህ ታሪክ ውስጥ እናየዋለን፡፡ ልክ እንደ አስቴር ሁሉ ኢየሱስም ጅምሩ ላይ ማን እንደሆነ ራሱን አልገለጠም ነበር፡፡ አስቴር ራሷን ዝቅ አድርጋ ከህዝቧ ጋር እንደ ተቆጠረች ኢየሱስም በሰውነቱ በነገር ሁሉ እንደ እኛ ስለሆነ በዚህም እንደ እኛ ስለተቆጠረ የነገስታት ንጉስ በሆነው ፊት ስለ እኛ ይማልዳል፡፡
ምናልባት አሁን ባለህበት ሁኔታ እግዚአብሔር እያለፍክበት ያለህበትን ጎዳና የማያይና ለአንተም ግድ እንደሌለው ይሰማህ ይሆናል፡፡ አሁን ምንም ዓይነት ሁኔታ እየገጠመህ ይሁን ነገር ግን አንድ ነገር ልብ በል እርሱም ኢየሱስ በየትኛውም መንገድ ከአንተ ጋር መሆኑን እወቅ፡፡
Scripture
About this Plan

የአስቴር መጽሐፍ የእግዚአብሔር ህዝብ ከዘር ወይም ከጅምላ ጥፋት ራሱን ሊከላከል እንኳን አቅም እንደሌለው በግልፅ ያሳያል፡፡ ራሷን አደጋ ውስጥ ጥላ ስለ ህዝቡ በንጉሱ ፊት ለመቆም ከህዝቡ ጋር በመሆን ራሷን ለየች:: ይህ የሶስት ቀናት የንባብ ዕቅድ የአስቴርን የጥንካሬና ፍቅር ታሪክ የሚዳስስና የክርስቶስን ታሪክ የሚያንፀባርቅ ሲሆን ይኸውም እርሱ እንደ እኛ ተቆጠሮ፣ ስለ እኛ መካከለኛ ሆኖ እና እኛ ራሳችንን ማዳን በማንችልበት ሁኔታ አዳነን፡፡
More
Related Plans

Raising People, Not Products

Unapologetically Sold Out: 7 Days of Prayers for Millennials to Live Whole-Heartedly Committed to Jesus Christ

Principles for Life in the Kingdom of God

Restore: A 10-Day Devotional Journey

Horizon Church August Bible Reading Plan: Prayer & Fasting

Evangelistic Prayer Team Study - How to Be an Authentic Christian at Work

RETURN to ME: Reading With the People of God #16

Presence 12: Arts That Inspire Reflection & Prayers

Overcoming Spiritual Disconnectedness
