YouVersion Logo
Search Icon

በየእለቱ ከእግዚአብሔር መስማትSample

 በየእለቱ ከእግዚአብሔር መስማት

DAY 8 OF 14

የእግዚአብሔርን ፀሎት መፀለይ

ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው፡፡ ኢሣ 55:9

እንደሚመስለኝ ከሆነ አንዳንድ ጊዜ በፀሎታችን የማንረዳውና ፀሎን ያለመጨረስ ስሜት የሚሰማንና ረዥም ሰዓት በመውሰድ በጉዳያችንና በችግራችን ዙሪያ የእራሳችንን ፀሎት ስለምንፀልይ ነው፡፡

ነገር ግን እውነቱን ስነግርህ ጥሩ የሆነ ከፍ ያለና በጣም ውጤታማ መንገድ እግዚአብሔራዊ ፀሎት መፀለይ ነው፡፡ እርግጠኛ እንድሆን ልክ እኔ በሕይወቴ የእራሴን ፀሎት በምፀልይበት ወቅት ስለ አንድ ጉዳይ ለአሥራ አምስት ደቂቃ እፀልይና አሁንም የጨረስኩ አይመስለኝም፡፡ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ተመርቼ በምፀልይበት ወቅትና የእግዚአብሔር ፀሎት ስፀልይ ሁለት ዓረፍተ ነገር ብቻ እፀልይና እረካለሁ፡፡

እኔ በሕይወቴ እንዳየሁት መንፈስ መሪ የሆነ ፀሎት ስፀልይ ፀሎቴ አብዛኛውን ጊዜ ቀላልና አጭር ነው፡፡ እኔ በራሴ ከምፀልየው ይልቅ መንፈስ ቅዱስ መሪ የሆነ ፀሎት ቀጥተኛ ፊት ለፊት ዋና ጉዳይ ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ የእኔ የሆነ ፀሎት ትቼ እግዚአብሔራዊ ፀሎት ስፀልይ ጉዳዩ እንዳለቀና እንደተጠናቀቀ ስለሚሰማኝ እርካታ ይሰማኛል፡፡

በራሳችን መንገድ ስንጸልይ ፣ ብዙውን ጊዜ ለሥጋዊ ነገሮች እና ሁኔታዎች መጸለይ ላይ እናተኩራለን ፣ ግን በእግዚአብሔር የምንመራ ከሆነ እንደ ሀሳባችን እና እንደ ዓላማችን ንፅህና እና ከእግዚአብሄር ጋር ጥልቅ ግንኙነትን ስለማድረግ በመፀለይ ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር የራስህን ፀሎት ከመፀለይ የእርሱን ፀሎት መፀለይ እንዳለብን እንዲያስተምርህ ጠይቀው፡፡

ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል: የእራስህን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፀሎት ፀልይ፡፡

Scripture

About this Plan

 በየእለቱ ከእግዚአብሔር መስማት

ይህ አምልኳዊ አገልግሎት ከእግዚአብሄር ጋር አብዛኛውን ጊዜዎን እንዲጠቀሙ እና ከእግዚአብሔር ጋር የበለጠ የግል ጊዜን በማሳለፍ ግንኙነቶችዎን እንዲያሳድጉ እርስዎን ለማነሳሳት እና ለማበረታታት የሚያስችሉ ማስታወሻዎችን ይሰጣል።

More