1
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ ዓላማውም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
比較
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28で検索
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:38-39
ይህንን ተረድቼአለሁ፤ ሞትም ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ገዢዎችም ቢሆኑ፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ጥልቀትም ቢሆን፥ ሌላ ፍጥረትም ቢሆን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:38-39で検索
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:26
እንዲሁም ደግሞ መንፈስ በድካማችን ይረዳናል፤ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በቃላት ሊገለጥ በማይችል መቃተት ለእኛ ያማልድልናል፤
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:26で検索
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:31
እንግዲህ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:31で検索
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:1
ስለዚህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:1で検索
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:6
ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:6で検索
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:37
በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:37で検索
8
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:18
የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ወደ ፊት ለእኛ ከሚገለጥልን ክብር ጋር ሲነጻጸር ምንም ዋጋ እንደሌለው እቆጥረዋለሁ።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:18で検索
9
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:35
ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማን ነው? መከራ ወይስ ሥቃይ፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ረሃብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ አደጋ፥ ወይስ ሰይፍ?
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:35で検索
10
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:27
ልቦችንም የሚመረምረው እርሱ የመንፈስ ሐሳብ ምን እንደሆነ ያውቃል፥ ምክንያቱም መንፈስ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ያማልዳልና።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:27で検索
11
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:14
በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ፥ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:14で検索
12
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:5
እንደ ሥጋ የሚኖሩ አእምሮአቸው የሥጋን ነገር እንዲያስብ ያደርጋሉና፥ እንደ መንፈስ የሚኖሩ ግን አእምሮአቸው የመንፈስን ነገር እንዲያስብ ያደርጋሉ።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:5で検索
13
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:32
ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው እርሱ፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:32で検索
14
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:16-17
የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን መንፈሱ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክርልናል። ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ከእርሱ ጋር የክብሩ ተካፋዮች እንድንሆን ከእርሱ ጋር መከራ ብንቀበል የእግዚአብሔር ወራሾችና ከክርስቶስም ጋር አብረን ወራሾች ነን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:16-17で検索
15
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:7
ስለ ሥጋ ማሰብ የእግዚአብሔር ጠላት መሆን ነው፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም አይችልም፥
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:7で検索
16
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:19
ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ በታላቅ ናፍቆት ይጠባበቃልና።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:19で検索
17
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:22
እስከ አሁን ድረስ ፍጥረት ሁሉ አብሮ በመቃተትና በምጥ ሥቃይ እንደሚኖር እናውቃለንና።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:22で検索
ホーム
聖書
読書プラン
ビデオ