YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ ኢዮብ 25

25
1ሹሐዊውም በልዳዶስ መለሰ እንዲህም አለ፦
2ገዢነትና መፈራት በእርሱ ዘንድ ናቸው፥
በከፍታውም ሰላም አድራጊ ነው።
3በውኑ ለሠራዊቶቹ ቍጥር አላቸውን?
ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው?
4ሰውስ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ይሆን ዘንድ፥
ከሴትስ የተወለደ ንጹሕ ይሆን ዘንድ እንዴት ይችላል?
5እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ብሩህ አይደለም፥
ከዋክብትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም።
6ይልቁንስ ብስብስ የሆነ ሰው፥
ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in