መዝሙረ ዳዊት 126
126
የመዓርግ መዝሙር።
1እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥
ቤትን የሚሠሩ በከንቱ ይደክማሉ፤
እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥
የሚጠብቁ በከንቱ ይተጋሉ።
2በማለዳ መገሥገሣችሁም ከንቱ ነው።
ለወዳጆቹ እንቅልፍን በሰጠ ጊዜ፥
እናንተ የመከራን እንጀራ የምትበሉ፥
ከተቀመጣችሁበት ተነሡ።
3እነሆ፥ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፥
የሆድም ፍሬ የእርሱ ዋጋ ነው።
4በኀያል እጅ እንዳሉ ፍላጾች፥
የተጣሉ ሰዎች#ዕብ. “የጐልማሳነት” ይላል። ልጆች እንዲሁ ናቸው።
5ከእነርሱ ዘንድ ምኞቱን የሚፈጽም ሰው ብፁዕ ነው፤
ጠላቶቹን በአደባባይ በተናገረ ጊዜ እርሱ አያፍርም።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 126: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in