YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ ሲራክ 49

49
ኢዮስያስ
1 # 2ነገ. 22፥1፤ 22፥11-13፤ 23፥3፤25። የኢዮስያስ ትውስት፥ በሽቶ ጠማቂው ጥበብ እንደተቀመጠ ዕጣን መዓዛው አይጠፋም፥ ለሁሉም አፎች እንደ ማር የሚጣፍጥ፥ በወይን ጠጅ ግብዣም ላይ እንደሚሰማ ጣዕመ ዜማ ነው። 2ሕዝቡን ለመለወጥ ትክክለኛውን መንገድ መርጧል፥ አስከፊ የሆኑትን በደሎችም ነቃቅሎ ጥሏል። 3ልቡን በጌታ ላይ አሳረፈ፤ በክሕደት ወቅት ለሃይማኖት በጽናት ተሟገተ፥ የመጨረሻዎቹ ነገሥታትና ነቢያት፥ 4ከዳዊት፥ ከሕዝቅያስና ከኢዮስያስ በቀር፥ ሁሉም ጥፋትን በጥፋት ላይ ከመሩ፥ የልዑል እግዚአብሔርን ሕግ ዘነጉ፤ የይሁዳ ነገሠታት ጠፉ። 5ሥልጣናቸውን ለሌሎች፥ ክብራቸውንም ለውጭ፥ መንግሥታት አሳልፈው ሰጥተዋልና። 6#ኤር. 1፥4-10፤ 39፥8።የተመረጠችው ቅድስት ከተማ በእሳት ጋየች፤ መንገዶቿ ባዷቸውን ቀሩ። 7በእናቱ ማሕፀን ሳለ ለነቢይነት የተቀደሰ ቢሆንም፥ ለመቆራረጥ፥ ለማሠቃየት፥ ለማጥፋት ብቻ ሳይሆን፥ ለመገንባትና ለመትከል ቢመረጥም፤ እነርሱ ግን በድለውታልና ኤርምያስ ይህን ቀድሞ ተንብዮአል። 8#ሕዝ. 1፥3-15፤ 14፥14-20።አምላክ ከታላላቆቹ፥ ከኪሩቤልና ከሱራፌል ሠረገላ በላይ፥ ያሳየውን የክብር ራእይ ያየው ሕዝቅኤል ነበር። 9ዶፍ የወረደባቸውን የጠላት ወታደሮች በመጥቀሱ ትክክለኛውን መንገድ የተከተሉትን ጠቅሟልና። 10ዐሥራ ሁለቱን ነቢያት በተመለከተ ደግሞ ያዕቆብን በማጽናናታቸው እና በተስፋና በእምነትም እርሱን በመቤዣቸው አጥንታቸው ከመቃብር በላይ ዳግም ያብብ።
ዘሩባቤልና ኢያሱ
11 # ዕዝ. 3፥2፤ ሐጌ 2፥23። ዘሩባቤልን እንደምን ከፍ ከፍ እናድርገው? በቀኝ እጅ እንደሚደረግ የቀለበት ማኀተም ነበር፥ 12#ሐጌ 1፥1፤12።የዩሴዴቅ ልጅ ኢያሱም እንዲሁ ነበር። በኖሩበትም ዘመን የእግዚአብሔርን ቤት አሠሩ፥ ዘላለማዊ ክብር ያለውን፥ ለእግዚአብሔር የተቀደሰውንም ቤተ መቅደስ አቆሙ። ነህምያ 13#ነህ. 6፥15።የነህምያ መታሰቢያው ታላቅ ነው፥ የፈረሰውን ግንብ የገነባ፥ ባለ ቁልፍ መዝጊያዎችን የሠራ፥ ቤቶቻችንንም ዳግም ያነጸ እርሱ ነው።
ትውስታ
14ሄኖክን የሚስተካከል በምድሪቱ አልተፈጠረም፥ እርሱ ከመሬት ተወስዷልና። 15እንደ ዮሴፍ የመሰለም ከዚህ በፊት አልተወለደም የወንድሞቹ መሪ፥ ሕዝቡንም የደገፈ ነውና፥ አጥንቶቹ መጐብኘትን አግኝተዋል። 16ከሰዎች ሁሉ የተከበሩት ሴምና ሴት ነበሩ፥ ከሁሉም ሕያው ፍጡር የበለጠው ግን አዳም ነው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in