መጽሐፈ ሲራክ 45
45
ሙሴ
1 #
ዘፀ. 6፥28—11፥10፤ 20፥1-21። ከያዕቆብ ዘር አንድ ደግ ሰው ፈጠረ፤ እርሱም በሰዎች ዘንድ ተወዳጅነትን አገኘ፤ በእግዚአብሔርና በሰዎች ዘንድ የተወደደው፥ የሙሴ መታሰቢያው የተባረከ ነው። 2ከቅዱሳን ጋር የሚተካከል ክብር፥ ጠላቶቹንም የሚያሸብር ብርታት ሰጠው። 3በሙሴ ቃል ድንቅ ነገሮችን ተወ፥ በነገሥታትም ፊት ከፍ ከፍ አደረገው። ሕዝቡ የሚፈጽሟቸውን ትእዛዛት ሰጠው። ከክብሩም በከፊል አሳየው። 4በታማኝነቱና በደግነቱ ቀደሰው፤ ከሰዎችም ሁሉ መረጠው። 5ድምፁን እንዲሰማ ፈቀደለ፥ ወደ ጨለማውም መራው። 6#ዘፀ. 4፥14።ለያዕቆብ ሕጐቹን፥ ለእስራኤል አዋጆቹን ያስተምር ዘንድ፥ ትእዛዛቱን ፊት ለፊት ሰጠው።
አሮን
7 #
ዘፀ. 28፥1-43። ከሌዌ ነገድ የሆነ ወንድሙን፥ እንደ እርሱ የተቀደሰውን አሮንን አስነሣ። ከእርሱም ጋር ዘላለማዊ ቃል ኪዳን አደረገ፥ ሕዝቡን እንዲያገለግልም ክህነትን ሰጠው። በልብሰ ተክህኖ አንቆጠቆጠው፤ የክብርም ካባ አጐናጸፈው። 8ታላቅነትን አለበሰው፥ ውድ የሆኑ ጌጦች፥ ሱሪ፥ ቀሚስና ካባም ሸለመው። 9በቀሚሱ ዙሪያ የሚደረግ የሮማን መርገፍ፥ እርሱ በተራመደ ቍጥር የሚያቃጭሉ፥ ቤተ መቅደሱን በድምፃቸው የሚሞሉ፥ የሕዝቦች ልጆች መታሰቢያ የሆኑ፥ የወርቅ ደውሎችንም ሰጠው። 10በጌጥ የተሠራ የተቀደሰ የወርቅ ልብስ፥ በአዋቂ የተሠራ ወይን ጠጅ ከፋይ፥ ጠቢብ የሠራቸው የተጐነጐኑ የቀያይ የፍርድ ሜዳልያዎች፥ 11በወርቅ የተለበጡ ጠቢብ የሠራቸው፥ እንደ ማኀተም የተቀረጹ የክብሩ ደንጊያዎች፥ የእስራኤልን ነገዶች ቍጥር በውስጣቸው የያዙ መታሰቢያዎች፥ 12ለዐይን ደስ የሚያሰኝ የቅድስና ማኀተም የተቀረጸበት፥ እጅግ ያጌጠና የድንቅ ሥራ ውጤት የሆነ፥ በጥምጥሙ ላይ የሚያርፍ የወርቅ አክሊልም ሰጠው። 13ከእርሱ በፊት ይህን የመሰለ ውብ ነገር ከቶ አልነበረም፥ ከእርሱም በኋለ ከልጆቹና ከወገኖቹ በቀር፥ ማንም ቢሆን ጨርሶ አልለበሳቸውም። 14መሥዋዕቶቹም በቀን ሁለት ጊዜ የሚቀርቡ፥ የማይቋርጡና ሙሉ በሙሉም የሚቃጠሉ ነበሩ። 15#ዘሌ. 8፥1-36።ሙሴ ቀደሰው፥ በቅዱሱም ዘይት ቀባው፥ ይህም ለእርሱና ለወገኖቹም ጭምር፥ እስከ ሕልፈተ ሰማይ የገባው ቃል ኪዳን ነው፥ የአምልኮውን ሥርዓት እንዲመራ፥ ካህን ሆኖም በእግዚአብሔር ስም ሕዝቡን እንዲባርክ ሥልጣን ሰጠው። 16ለሕዝቡ ኃጢአት ስርየት ዕጣንና ሽቶን በመታሰቢያነት፥ መሥዋዕቶችንም ለጌታ ያቀርብ ዘንድ፥ ከነበሩት ሁሉ እርሱን መረጠው። 17ያዕቆብን ያስተምር፥ እሥራኤልንም በሕጉ ያሰለጥን ዘንድ፥ ትእዘዙን ሰጠው፥ ሕጉንም አስረከበው። 18#ዘኍ. 16፥1-35።ሌሎች ግን በእርሱ ላይ አሴሩ፥ በበረሃማ ሳሉ ተመቀኙት፥ ዳታን አቢሮንና ተከታዮቻቸው፥ ኮፊና ወገኖቹም ጭምር በቁጣ ተነስተውበታል። 19ጌታ ይህን ባየ ጊዜ አዘነ፥ በቁጣው ቀሰፋቸው። በእነርሱ ላይ ተአምራቱን ሠራ በእሳትም ነበልባል ፈጃቸው። 20የአሮንን ክብር ከፍ አደረገ፥ ውርስም ሰጠው፥ የመጀመሪያዎቹ ፍሬዎች የእርሱ ድርሻ እንዲሆኑ፥ ከሁሉም በፊት ያሻውን ያህል እንጀራ እንዲወስድም ፈቀደ። 21እነርሱም ለእርሱና ለዘሮቹ የፈቀደላቸውን የጌታን መሥዋዕቶች ይመገባሉ። 22#ዘኍ. 18፥20፤ ዘዳ. 12፥12።ከሕዝቡ ርስት ግን አይካፈልም፥ ያንተ ድርሻና ርስት እኔ ነኝ ባለው መሠረት ከሕዝቡ መካከል ድርሻ የሌለው እርሱ ብቻ ነው።
ፊንሃስ
23 #
ዘኍ. 25፥7-13። ጌታን በመፍራት ትጋቱ፥ ሕዝቡ ባመፀ ወቅት በእምነቱ በመጽናቱ፥ በልበ ሙሉነትና በድፍረት በመቆሙ፥ ለእሥራኤልም ስርየትን በማስገኘቱ፥ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስ ክብርን በተመለከተ በሦስተኛ ደረጃ ላይ ነው። 24ከዚህም የተነሣ፥ የቤተ መቅደሱና የሕዝቡ አለቃ ሆኖ ከመመረጡመ በላይ፥ እርሱና የእርሱ ወገኖች የክህነት እልቅናን ለዘለዓለምም ያገኙ ዘንድ ቃል ኪዳንን አገኙ። 25ከይሁዳ ነገድ ከእሴይ ልጅ፥ ከዳዊትም ጋር እንዲሁ፥ ከልጅ ወደ ልጅ ብቻ የሚተላለፍ የዙፋን ውርስ፥ ቃል ኪዳን ነበር። የአሮን ውርስ ግን ለወገኖቹ ሁሉ ይተላለፋል። 26የአባቶቻችሁ ደግነት እንዳይጠፋ፥ ወገኖቻቸውም ክብራቸውን እንዳወርሱ፥ ሕዝቡን በትክክል ታስተዳድሩ ዘንድ፥ እግዚአብሔር ልባችሁን በጥበብ ይሙላው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 45: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: